የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት የማተሚያ ማሽኖችን ከቅድመ ህትመት እስከ ድህረ ህትመት በዓለም አቀፍ የግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

ዓለም አቀፍ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 001/2018

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በ2018 በጀት ዓመት የማተሚያ ማሽኖችን ከቅድመ ህትመት እስከ ድህረ ህትመት (sheet fed offset press, folding machine, paper cutting machine, perfect binding machine, double saddle stitcher, laminating machine, heavy duty printer, Thermalctp) (ተከላ፣ ሥራ ማስጀመር፣ ሥልጠና እና ፍተሻን ጨምሮ በዓለም አቀፍ የግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም፡- ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።

  • በዘርፉ የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው
  • የንግድ ምዝገባ
  • የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት
  • የቫት ሰርተፍኬት
  • በመንግስት ግዥ በአቅራቢነት የተመዘገበ

ለጨረታ ማስከበርያ መጠን 500,000.00(አምስት መቶ ሺህ ብር) ወይንም በውጭ ሀገር መገበያያ ገንዘብ (የአሜሪካ ዶላር፣ የእንግሊዝ ፓውንድ፣ ወይም ዩሮ) በሲ.ፒ.ኦ ወይም ቢድ ቦንድ ወይም ለጥቃቅንና አነስተኛ ከአደራጃቸው አካል የሚሰጥ የዋስትና ደብዳቤ በማያያዝ ይህ ጨረታ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር 45 ተከታታይ ቀናት አንደኛ ፎቅ በሚገኘው አቅርቦት መምሪያ በተዘጋጀው የጨረታሳጥን ውስጥ ቴክኒካል ዶክመንት ዋና እና ቅጂ እንዲሁም የሚወዳደሩበትን ዋጋ ዋና እና ቅጂ በሚል በጉልህ በሚታይ መልኩ በመጻፍና የሚወዳደሩበትን በፖስታዎቹ ላይ በመግለጽ በአራት የተለያየ ፖስታ በማሸግ ማስገባት የሚኖርባቸው ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያ ቴክኒክ ዋና ሰነድ ፖስታ ውስጥ ተያይዞ መገኘት አለበት።

  • በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 45 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 100 ብር በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  • ስርዝ ድልዝ ያለውና ያልተፈረመ እንዲሁም በጉልህ የማይታይ አጠራጣሪ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።
  • ጨረታው በ46ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 4፡30 በኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት አቅርቦት መምሪያ 1ኛ ፎቅ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን የተጫራቹ አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉለውም። የጨረታ መክፈቻው ቀን እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣይ ባለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
  • ድርጅታችን አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡-አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት ፊት ለፊት

E-mail: procurement@press.et 

የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-08-04
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ46ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-08-04 10:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ46ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Press Agency
  • Buyer address: አራት ኪሎ ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት ፊት ለፊት
  • Bid bond: 500,000.00 ብር
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: Jun 20, 2026
  • Posted at: 2026-06-20T08:18:33.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders