በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን የሀብሩ ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት የግዥ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ለሀብሩ ወረዳ ባህል እና ቱሪዝም ጽ/ቤት የባህል ቡድን የሙያ አገልግሎት ግዥ በመደበኛ በጀት ከሀምሌ 01/2019 ዓ.ም ጀምሮ የወረዳውን የተለያዩ የልማት ስራዎች ለማስተዋወቅ፣ ግንዛቤ በመፍጠር እና ቱባ ባህልን በማውጣት የወረዳውን ገጽታ ለማንጸባረቅ የሚሰሩ

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 05/2019

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰሜን ወሎ ዞን የሀብሩ ወረዳ ገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ጽ/ቤት የግዥ ንብረት አስተዳደር ደጋፊ የስራ ሂደት ለሀብሩ ወረዳ ባህል እና ቱሪዝም ጽ/ቤት የባህል ቡድን የሙያ አገልግሎት ግዥ በመደበኛ በጀት ከሀምሌ 01/2019 ዓ.ም ጀምሮ የወረዳውን የተለያዩ የልማት ስራዎች ለማስተዋወቅ፣ ግንዛቤ በመፍጠር እና ቱባ ባህልን በማውጣት የወረዳውን ገጽታ ለማንጸባረቅ የሚሰሩ የተደራጁ የባህል ቡድኖች በዘርፉ የንግድ ስራ ፍቃድ ያላቸውን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆን ይጋብዛል።

1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው በተጠየቁት የአገልግሎት ግዥ አይነትና ዘርፍ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ።

2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin / ያላቸው

3. የአገልግሎት የግዥ መጠኑ ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።

4. በውሉ መሰረት ያሸነፈበትን አግልግሎት ማቅረብ የምችል

5. ማስታወቂያው አየር ላይ የሚቆይበት ጊዜ የባህል ቡድን የሙያ አገልግሎት ግዥ ፣በሀብሩ ወረዳ ባህል እና ትራንስፖርት ጽ/ቤት ስር በመደበኛ በጀት የባህል ቡድን የሙያ አገልግሎት ግዥ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እስከ 11፡30 የስራ ቀን ድረስ ብቻ ነው።

6. የጨረታውን ማስከበሪያ የባህል ቡድን የሙያ አገልግሎት ግዥ 8,000/ ስምንት ሺህ ብር/ በCPO ያሲዛሉ ወይም ገንዘቡን አስቀድሞ ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ኮፒ ፖስታ ውስጥ በማድረግ ያቀርባሉ።

7. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድና መመሪያ ለእያንዳዱ ለተጠየቀ ግዥ ሰነድ በማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን ዝርዝር ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰዓት ጨረታውን አየር ላይ ከዋለበት እስከ መጨረሻ ቀን እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 8 በመገኘት መግዛት ይችላሉ።

8. ተጫራቾች የጨረታው ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ኦርጅናል እና ኮፒ በማለት የሀብሩ ወረዳ ባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት የባሀል ቡድን የሙያ አገልግሎት ግዥ በ16ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ቢሮ ቁጥር 8 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

9. የጨረታ ሳጥኑ በ4፡00 ሰዓት ይታሸጋል የጨረታው ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚቀርብ የጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም።

10. የጨረታ ሳጥን የሚከፈትበት ቦታ ግዥ/ን/ብ/አስ/ደ/የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 8 የባህል ቡድን የሙያ አገልግሎት ግዥ በ16ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች እራሳቸው ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል ጨረታው የሚከፈትበት እለት የስራ ቀን ካልሆነ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው በተመሳሳይ ስዓት ታሽጎ የሚከፈት ይሆናል

11. ተጫራቾች በጨረታው አሸናፊ ከሆኑ 10% የውል ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተረጋገጠ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርብዎታል።

12. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈለጉ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 8 ድረስ በአካል በመገኘት ማግኘት ይችላሉ።

14. አሸናፊው የሚለየው በሎት ድምር ውጤት መሰረት ይሆናል።

የሐብሩ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-06
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-06 12:00
  • Bid opening (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: North Wollo Zone Habru Woreda F/E/D/Bureau
  • Bid bond: 8000.00 /ስምንት ሽህ ብር/
  • Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published: Jun 20, 2026
  • Posted at: 2026-06-20T08:24:05.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders