የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የአስፓልትና ውሃ መውረጃ ቦይ (ዲች) የጽዳት አገልግሎት ግዥ እና የአረንጓዴ ሥፍራዎችን እና የእግረኛ መንገድ አካፋይ ሳር መንከባከብ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር EEPNP/NCB/27/2018

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል

በሎት- 1 የአስፓልትና ውሃ መውረጃ ቦይ (ዲች) የጽዳት አገልግሎት ግዥ እና 

በሎት- 2 የአረንጓዴ ሥፍራዎችን እና የእግረኛ መንገድ አካፋይ ሳር መንከባከብ ለአንድ ዓመት የሚቆይ አገልግሎት ግዥ በዘርፉ ከተሰማሩ፤ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል።

 ስለሆነም ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩና አግባብነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት(TIN) ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢዎች ዝርዝር ድህረ-ገዕ (e GP) ላይ የተመዘገቡ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ መሆን አለባቸው።

2. በዚህ ጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች በማያያዝ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ዝርዝር ሁኔታው በጨረታ ሰነዱ ውስጥ ይገኛል፤

3. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት ኮተቤ ብረታ ብረት ፊት ለፊት በሚገኘው ዋናው መ/ቤት ህንፃ ቁጥር-11 1ኛ ፎቅ በሚገኘው ገንዘብ ተቀባይ ቢሮ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ) በመክፈል እና የጨረታ ሰነዱን ህንፃ ቁጥር-9 1ኛ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 201 በመምጣት መውሰድ ይችላሉ።

4. ተጫራቾች በሎት-1 የአስፓልትና ውሃ መውረጃ ቦይ (ዲች) የጽዳት አገልግሎት ግዥ እና በሎት-2 የአረንጓዴ ሥፍራዎችን እና የእግረኛ መንገድ አካፋይ ሳር መንከባከብ አገልግሎት ግዥ የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነዳቸውን ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ቁጥር EEP/NP/NCB/27/2018 የቴክኒካል እና ፋይናንሻል ሰነድ የሚል ምልክት በማድረግ ከታች በተቀመጠው ሰንጠረዥ መሠረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ቁጥር

የግዥ አይነት Description

የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ

የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት

ሎት 1

የአስፓልትና ውሃ መውረጃ ቦይ (ዲች) የጽዳት አገልግሎት ግዥ

 

ብር 12,000.00 (አሥራ ሁለት ሺህ ብር)

ሰኔ 22 ቀን 2018 .ከቀኑ800 ሰዓት

 

ሰኔ 22 ቀን 2018 . ከቀኑ 830 ሰዓት

 

 

ሎት 2

የአረንጓዴ ሥፍራዎችን እና የእግረኛ መንገድ አካፋይ ሳር መንከባከብ አገልግሎት ግዥ

215,000(ሁለት መቶ አሥራ አምስት ሺህ ብር)

5. ተጫራቾች ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 011-558-0627 መደወል ይችላሉ።

6. ገዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል


Tender details

  • Deadline: 2026-06-29
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-06-29 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Electric Power
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 1000 (አንድ ሺህ ብር)
  • Published: Jun 20, 2026
  • Posted at: 2026-06-20T08:39:11.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders