በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የአቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ የ Induction Furnace 3.3ton አስጠግኖ ወደ ስራ ለማስገባት በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግዥ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር: አቤሜኢ/ሰቼማ/ግጨ/2018/05

በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ የአቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ የ Induction Furnace 3.3ton አስጠግኖ ወደ ስራ ለማስገባት በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

  1. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የግብር መክፈያ ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥና በግብር ሰብሳቢ ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ቅጂ፣ አግባብ ያለው በዘርፉ የታደሰ  ንግድ ስራ ፍቃድ ቅጂውን፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት  እና የግብር መክፈያ መለያ ሰርተፍኬት ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው።
  2. የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00/ሦስት መቶ ብር/ በአቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ ስም ሒሳብ ቁጥር 1000014630906 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ-አርብ ጠዋት 2፡00-6፡00 ሰዓት ከሰአት 7፡00-11፡00 ሰዓት ኢንዱስትሪያችን ቅጥር ግቢ በመቅረብ ሰነዱን ከግዥ ከፍል መግዛት ይችላሉ።
  3. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 50,000.00 (ሀምሳ ሺህ ብር) በCPO ወይም bank guarantee ወይም Cash ቢያንስ ለ88 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  4. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ15ኛው ቀን 8:00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ በዚሁ እለት በ8:15 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 1ኛ ወለል ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 22 ውስጥ ይከፈታል።
  5. ጨረታው ከሚከፈትበት ቀን ጀምሮ ለ60 ቀናት ፀንቶ ይቆያል።
  6. ኢንዱስትሪው ጨረታውን በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  7. ቲክኒካልና ፋይናንሻል ለየብቻ ሆኖ በኢንቨሎፕ አሽጎ ዋናውና ኮፒውን ለየብቻ በማድረግ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባችሁ።

አድራሻ፦ ከአ/አ ወደ ዱከም መሄጃ መንገድ ላይ ከሚገኘው ሸገር ከተማ የፍተሻ ጣቢያ

(ኬላ) አጠገብ ከASTCO FOOD COMPLEX በቀኝ በኩል ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ ይገኛል።

ለተጨማሪ መረጃ:- ስልክ ቁጥር 011 434 0409/ 011 435 0608

በኢትዮ ኢንጂነሪንግ ግሩፕ

የአቃቂ ቤዚክ ሜታልስ ኢንዱስትሪ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-08
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ15ኛው ቀን 8:00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-08 14:15
  • Bid opening (note): ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት አየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ15ኛው ቀን 8:15 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethio Engineering Group Akakai Basic Metals Industry
  • Buyer address: ከአ/አ ወደ ዱከም መሄጃ መንገድ ላይ ከሚገኘው ገላን ከተማ ሳይደርስ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ የፍተሻ ጣቢያ (ኬላ) አጠገብ ከASTCO FOOD COMPLEX በቀኝ በኩል ሁለት መቶ ሜትር ገባ ብሎ
  • Bid bond: 50,000.00 ብር
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Jun 21, 2026
  • Posted at: 2026-06-22T09:36:09.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders