የቀይ ሽብር ሰማዕታት ቤተሰቦችና ወዳጆች ማህበር ተሽከርካሪ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
ውስን የጨረታ ሰነድ
የቀይ ሽብር ሰማዕታት ቤተሰቦችና ወዳጆች ማህበር በመስቀል አደባባይ ወደ ቦሌ በሚወስደው ዋና መንገድ በስተቀኝ በኩል በሆነው ቦታ ሙዚየም 1 ላንድ ክሩዘር መኪና ያገለገለ የተሸከርካሪው አይነት የመስክ ተሸከርካሪ የታርጋ ቁጥር 05-01020 የተሰራበት ሀገር ጃፓን፤ የተሽ/ሞዴA HZJ 80L-GNMNS፣ የተሰራበት ዘመን 1985፣ የሻንሲ ቁጥር HZJ 80 - 0003815 የሞተር ቁጥር IHZ0024489፣ የአካል ዓይነት የሕዝብ፣ ቀለም ካኪ፣ የነዳጅ ዓይነት ናፍታ፣ የሞተር የፈረስ ጉልበት 130 የተሽ/ጠቅ/ክብደት 3160፣ ነጠላ ክብደት 1960፤ የጭነት መጠን 4 ሰው የሞተር ችሎታ /ሲሲ/4164፣ የሲሊንደር ብዛት 6፣የተፈቀደለት የሥራ ፀባይ ለኮድ 5 አገልግሎት፣ የአክስል ብዛት የፊት-የኋላ 1-1 የሆነ ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የሚከተለውን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- 2017 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ የግብር መለያ (TIN) ሰርተፊኬት የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ከሆኑ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ታክስ ከከፈሉበት የገቢዎች ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የተሰጠ ሰርተፊኬት ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለጨረታ ያቀረቡትን አጠቃላይ ዋጋ 15% ፐርሰንት ለቀይ ሽብር ሰማዕታት ቤተሰቦችና ወዳጆች ማህበር ስም በተዘጋጀውና በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20 ቀን ድረስ ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታ ሰነዱን መስቀል አደባባይ በሚገኘው የቀይ ሽብር ሰማዕታት ቤተሰቦችና ወዳጆች ማህበር ሙዚየም የማይመለስ 2000 ብር ሰነድ ( ሁለት ሺ ብር) በመግዛት በዋናው መ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሰነዳችሁን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊው ተጫራቾች የመንግስት ዕዳ እና የመንገድ ትራንስፖርት የስም ማዛወሪያ ገንዘብ ይሸፍናል።
- እራሳቸው ተጫራቾች ያቀረቡትን ፕሮፎርማ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጥዋቱ 5፡00 ይከፈታል።
- ተጫራቾች ስለጨረታው ማብራሪያ ከፈልጉ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ 0911- 652817 በመደወል ማግኘት የሚችሉ መሆኑን እገልፃለን።
- የቀይ ሽብር ሰማዕታት ቤተሰቦችና ወዳጆች ማህበር የተሻለ አማራጭ ካገኝ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝመብቱ የተጠበቀ ነው።
- በጨረታው አሸናፊ የሆነው ተጫራች ተለይቶ ከታወቀ በኋላ በ15 ቀን ጊዜ ውስጥ የሺያጭ ውሉን ፈጽሞ ገንዘቡን ገቢ ካደረገ መኪናውን ማንሳት ይኖርበታል።
- በጨረታው አሸናፊ የሆነው ተጫራች የሺያጭ ውሉን በ15 ቀን ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ውል ካልፈፀመ ያስያዘው 15% ፐርሰንት የማይመለስ ይሆናል።
Tender details
- Deadline: 2026-07-10
- Bid closing time: 16:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20 ቀን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 10 ሰዓት
- Bid opening: 2026-07-11 11:00
- Bid opening (note): እራሳቸው ተጫራቾች ያቀረቡትን ፕሮፎርማ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጥዋቱ 5፡00 ይከፈታል
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Red Terror Martyrs Memorial Association
- Bid bond: 15%
- Bid document price: 2000.00 ብር
- Published: Jun 21, 2026
- Posted at: 2026-06-22T10:04:41.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.