በወላይታ ልማት ማህበር ዳሞታ ኮንስትራክሽን ኩባንያ ለሚያሠራቸው ግንባታ ሥራዎች ግንባታ ጥሬ ዕቃ የጥርብ ድንጋይ፣ የክስካሶ ድንጋይ፣ አሸዋ እና ጠጠር ከሚያቀርቡ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

በወላይታ ልማት ማህበር ዳሞታ ኮንስትራክሽን ኩባንያ በወላይታ ዞን ውስጥ በተለያዩ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ለሚያሠራቸው ግንባታ ሥራዎች ግንባታ ጥሬ ዕቃ የጥርብ ድንጋይ፣ የክስካሶ ድንጋይ፣ አሸዋ እና ጠጠር ከሚያቀርቡ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

በዚህም መሠረት በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ማቅረብ ያለባቸው፦

1. በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት

2. የታደሰ ሕጋዊ ንግድ ፍቃድ

3. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር

4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ምስክር ወረቀት

5. ሕጋዊ የሆነ ታክስ ክልራንስ

6. ቢያንስ 01 (አንድ) 16 ሜ.ክውብ መጫን የሚችል መኪና ሊብሬ ወይም ሕጋዊ የባለቤትነት ውክልና ማቅረብ የሚችል

7. የግንባታ ግብአቶችን ወደ ሳይት በተፈለገው ጊዜ በሚፈለገው ጥራትና መጠን ማቅረብ የሚችል

8. የጨረታ ማስከበርያ በCPO ብቻ ብር 40,000.00 (አርባ ሽህ ብር ብቻ) ማቅረብ የሚችል

9. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በአድስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15/አሥራ አምስት ቀናት ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከሁለተኛው መግቢያ በር ፊት ለፊት ከሚገኘው ከዩኒቨርሲቲ መምህራን መኖሪያ(ኮንዶሚኒየም) በስተጀርባ ከሚገኘው ዳሞታ ኮንስትራክሽን ኩባንያ ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ክፍል ዘውትር በሥራ ሰዓት የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጥሬ ዕቃዎቹን ዝርዝር መረጃ የያዘውን የዋጋ ማቅረብያ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።

10. ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያና ቴክንካል ሰነድ ዋናውን(ኦሪጅናሉን) አንድ ላይ በማሸግ እና የዋጋ ማቅረቢያና ቴክንካል ሰነድ አንድአንድ ኮፒ በሌላ ፖስታ በማሸግ የድርጅቱን ስምና አድራሻ በመጻፍ እና ሕጋዊ ማህተምና ፊርማ በማድረግ በወላይታ ልማት ማህበር ዳሞታ ኮንስትራክሽን ኩባንያ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ሥራ ክፍል በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

11. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአድስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15/አሥራ አምስት/ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኃላ ቀጥሎ በሚዉለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡30 ላይ ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 9፡00 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታ ሂደቱን አያስተጓጉልም።

12. ኩባንያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር፡-046 180 1798/ 046 180 1509 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል
አድራሻ፡- ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ከሁስተኛው መግቢያ በር ፊት ለፊት ከሚገኘው ከዩኒቨርሲቲ መምህራን መኖሪያ(ኮንዶሚኒየም) በስተጀርባ ከሚገኘው ዳሞታ ኮንስትራክሽን ኩባንያ ጽ/ቤት
ወላይታ ልማት ማኀበር ዳሞታ ኮንስትራክሽን ኩባንያ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-07
  • Publishing entity: Wolayita Development Association Damota Construction Company
  • Bid bond: 40,000.00 (አርባ ሽህ ብር)
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • Published: Jun 22, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders