በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው እቃዎች በሃራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

ሃራጅ ጨረታ ቁጥር ሃ-21/2018ዓ.ም.

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ብዛት ያላቸው

  • ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ እቃዎች) ፣
  • አዳዲስ አልባሳት፣
  • የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
  • ኮስሞቲክስ፣
  • ምግብ ነክ፣
  • Construction Material እና
  • Poly(Ethylene Verphthalate Plastic cas) ጥሬ ፕላስቲክ በሃራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ማሳሰቢያ፡- ጨረታው ሙሉ በሙሉ የሚከናወነው በኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ብቻ ሲሆን መተግበሪያውንም ከአፕ ስቶር ወይም ፕሌይ ስቶር (Auction Ethiopia) ብለው በማውረድ ወይም www.auction.et  ላይ መመዝገብ እና መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን፤ በዚህም መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ መስፈርቶች የምታሟሉ ግለሰብም ሆነ ድርጅቶች በጨረታው መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

1. ለጨረታ በቀረቡት እቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ  ከሚሸጠው እቃ ጋር ተዛማጅነት ያለው የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ እንቅስቃሴዎችን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው፤ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥሩን እንዲሁም ሰነድ የገዙበትን ደረሰኝ ጨምሮ በኦክሽን ኢትዮጵያ ኦንላይን መተግበሪያ ላይ ማያያዝ ይኖርባቸዋል። ማንኛውም ተጫራች 100 ብር በመክፈል ከኦክሽን ኢትዮጵያ መተግበሪያ ላይ የጨረታ ሰነድ ማግኘት ይችላሉ።

2. በተራ ቁጥር 1 ላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ቢኖርም መነሻ ዋጋቸው ከ500,000 (አምስት መቶ ሺህ) ብር በታች የሆነ እቃዎችን ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አያስፈልግም።

3. የጨረታ ሰነዱን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ የእቃዎቹን ዝርዝር፣ ዓይነት እና ብዛት የያዘውን ሰነድ የኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ ከንብረቶቹ መግለጫ ስር ተያይዞ የሚገኝ ስለሆነ አውርደው መመልከት ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች ኦክሽን ኢትዮጵያ ላይ ተመዝግበው የጨረታ ሰነዱን ካገኙ በኋላ ንብረቶቹን በአካል ለመመልክት ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን በስራ ሰዓት እና ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት መመልከት ይቻላል።

4. ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የሚወጣበት ቀን እንዲሁም ጨረታው የሚያበቃበት ቀን እና ሰዓት የሚያሳይ ሰንጠረዥ፡-

.

የእቃው ዓይነት

የጨረታው ዓይነት

በአዲስ ዘመን ጋዜጣ የታተመበት ቀን

ጨረታው የሚካሄድበት ቀን

ጨረታው የሚጀመርበት ሰዓት

ጨረታው የሚከፈትበት ሰዓት

ስልክ ቁጥር

1

አዳዲስ አልባሳት

ሃራጅ

15/10/2018

20/10/2018

4:00

8:00

022-111-8429

022-211-8925

 

2

ኤሌክትሮኒክስ

ሃራጅ

15/10/2018

20/10/2018

4:00

8:00

3

ኮስሞቲክስ

ሃራጅ

15/10/2018

20/10/2018

4:00

8:00

4

Poly (Ethylene Terphthalate)

ሃራጅ

15/10/2018

20/10/2018

4:00

8:00

5

ምግብ ነክ

ሃራጅ

15/10/2018

20/10/2018

4:00

8:00

6

Construction Material

ሃራጅ

15/10/2018

20/10/2018

4:00

8:00

7

ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ)

ሃራጅ

15/10/2018

20/10/2018

4:00

8:00

5.በሃራጅ ጨረታ ለምትወዳደሩ ለጨረታው ዋስትና የሚሆንማለትም፣

  • ለምድብ 01 ሸቀጣሸቀጥ (ልዩ ልዩ) ብር 77,800.00፤
  • ለምድብ 02 ሸቀጣሸቀጥ(ልዩ ልዩ) ብር 12,900.00፣
  • ለምድብ 03 ኤሌክትሮኒክስ ብር 211,200.00፣
  • ለምድብ 04 ኤሌክትሮኒክስ ብር 67,500.00፣
  • ለምድብ 05 poly(ethylene terephtalate) plastic cas(ጥሬ ፕላስቲክ) ብር 67,600.00 ለምድብ 06 ሸቀጣሸቀጥ(ልዩ ልዩ) ብር 33,300.00፣
  • ለምድብ 07 ሸቀጣሸቀጥ(ልዩ ልዩ) ብር 191,500.00፣
  • ለምድብ 08 ኮስሞቲክስ ብር 110,200.00፣
  • ለምድብ 09 ኮስሞቲክስ ብር 114,000.00፣
  • ለምድብ 10 ኮስሞትክስ ብር 406,400.00፣
  • ለምድብ 11 ኮስሞቲክስ ብር 116,000.00፣
  • ለምድብ 12 የኮንስትራክሽን ማቴሪያል ብር 213,500.00
  • ለምድብ 13 ኮስሞቲክስ ብር 849,300.00፤
  • ለምድብ 14 ኤሌክትሮኒክስ ብር 219,200.00፣
  • ለምድብ 15 ኮስሞቲክስ ብር 18,300.00፤
  • ለምድብ 16 ኮስሞቲክስ ብር 1,800.00
  • ለምድብ 17 ሸቀጣሸቀጥ(ልዩ ልዩ) ብር 203,400.00፣
  • ለምድብ 18 አዳዲስ አልባሳት ብር 537,000፣
  • ለምድብ 19 ኤሌክትሮኒክስ ብር 167,300፣
  • ለምድብ 20 ኮስሞቲክስ ብር 201,200፣
  • ለምድብ 21 ምግብ ነክ ብር 100፣
  • ለምድብ 22 ኤሌክትሮኒክስ ብር 1,439,100፣
  • ለምድብ 23 ኤሌክትሮኒክስ ብር 24,900 እና
  • ለምድብ 24 ኤሌክትሮኒክስ ብር 7,600(Customs Commission Adama Branch)

ስም ብቻ ሲ.ፒ.ኦ. በማሰራት ያሰሩትንም ሲ.ፒ.ኦ. በአካል ወደ ኦክሽን ኢትዮጵያ ቢሮ ሄደው በማስያዝ ወይም በኦንላይን ኦክሽን ኢትዮጵያ ፕላትፎርም ላይ በማስያዝ የሚጫረቱበትን ዋጋ ማስገባት ይችላሉ።

6. በሃራጅ ጨረታ ለመሸጥ የወጡት እቃዎች በአዳማ ከተማ በሬቻ አካባቢ መ/ቤቱ በተከራየው የውርስ መጋዘን ቁጥር 1 እና 2 ውስጥ ስለሚገኙ ለሃራጅ ጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ከዋለ በኋላ በስድስተኛው ቀን በኦክሽን መተግበሪያ ላይ በተሰጠው ሰዓት መሰረት ጨረታው ይካሄዳል።

7. በጨረታው ሽያጭ የእቃዎቹ አስመጪ ቤተሰብ ወይም ባለቤት የሆኑ ሰዎች መሳተፍ  አይችሉም። ነገር ግን በጨረታው ተሳትፈው ቢገኙ በህግ ተጠያቂ ይሆናሉ።

8. አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት CPO ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር ተደምሮ የሚታሰብላቸው ሲሆን፤ ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ3 /ሶስት/ የስራ ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

9. አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በማስታወቂያ ከተገለፀላቸው ቀን ጀምሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ እቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።

10. ከላይ በተ/ቁ 9 ላይ በተገለፁት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት (CPO) ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ እቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

11. ለጨረታ የቀረቡት እቃዎች ሽያጫቸው የሚፈፀመው ባሉበት ሁኔታ ስለሆነ ተጫራቾች ሌላ ተመሳሳይ ወይም ተጨማሪ እቃ መጠየቅ አይችሉም።

12. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ  መብቱ የተጠበቀ ነው።

13. ለጨረታ ማስከበሪያ የምታሰሩት CPO ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ መሆን እንዳለበት እና የሌላ ባንክ የማንቀበል መሆኑን እናሳስባለን።

N.B፡- በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለፁትን መረጃዎችን ያላሟላ ተጫራች ቢያሸንፍ

ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘውን ሲ.ፒ.ኦ ለመንግስት ገቢ የምናደርግ እና እቃው በድጋሜ  ጨረታ ላይ የሚወጣ መሆኑን እናሳውቃለን።

የኦክሽን ኢትዮጵያን መተግበሪያ በተመስከተ የጥሪ ማዕከሉን ለማግኘት በስልክ

መስመር 09-05-11-55 11/ 011-666 8828 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

ለተጨማሪ መረጃ፡- የአዳማ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የውርስ መጋዘን የስራ ሂደት ስልክ

ቁጥሮች 022 111 8429 እና 022 211 8925 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

ኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የአዳማ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-27
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-06-27 14:00
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Adama Custom Commission Branch Office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: Jun 22, 2026
  • Posted at: 2026-06-23T09:24:12.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders