የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት ንብረት ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ እጅ በእጅ በካሽ ወይም በከፊል ብድር ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ግልጽ የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 እና 1147/2011 መሠረት ተረክቦ ሁለት ጊዜ ሐራጅ ወጥቶ ሳይሸጥ የቀረውንና ባንኩ በቋሚነት የተረከበውን ንብረት ባለበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ እጅ በእጅ በካሽ ወይም በከፊል ብድር ለመሸጥ ይፈልጋል።

ተ.ቁ

የተበዳሪው የመያዝ ሰጪ/ስም

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

መያዥ ንብረት ዝርዝር መረጃ

ቀሪ የመሬት  (በዓመት)

የጨረታ መነሻ (ብር)

የጨረታው ደረጃ

ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት

1

ኤም ኤ ኢንተርናሽናልቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ማ እርሻ ልማት ድርጅት

በጋ/ሕ/ብ/ክ/መንግስት አኙዋ ዞን፣ ጋምቤላ ወረዳ፣ሶለን ቀበሌ 

500 ሄክታር የእርሻ መሬት (390 ሄክታር ማ።)

38

33,047,344.67

 

ግልጽ ጨረታ

 

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት ጽ/ቤት ሐምሌ 15 ቀን 2018 . 830-1030 ሰዓት

 

መጋዘን፣ ቢሮ፣ የሠራተኛ መኖሪያ፣ ካፈቴሪያና ሌሎች ግንባታዎች፡፡

የእርሻ መሳሪያ (LANDINI ትራክተሮች ሞዴል DT100 እና DT125 የተመረተበት ዘመን 2014 እና 2015)

ተሽከርካሪዎች (ISUZU የጭነት መኪና እና TOYOTA ባለ ሁለት ጋቢና ፒከአፕ፣ የተመረተበት ዘመን 2014 እና 2015)

የጨረታ መመሪያ

  1. በድርጅት ስም የሚጫረቱ ተጫራቾች የድርጅቱን የታደሰ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት፣ የንግድ ፈቃድ፣ የቲን (TIN) ቁጥር እና በሕግ የተረጋገጠ ውክልና እንዲሁም ማንነትን የሚገልጽ መታወቂያ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  2. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ ወይም 25% (ሃያ አምስት በመቶ) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (CPO) በማቅረብ መሳተፍ ይችላሉ።
  3. ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው የመንግሥት አካል የድጋፍ ደብዳቤ ይጽፋል።
  4. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 (አሥራ አምስት) የሥራ ቀናት ውስጥ አጠቃልሎ መክፈል ይኖርበታል። ካልከፈለ ግን ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል።
  5. በጨረታው ላላሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።
  6. አሸናፊው 15% ተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የስም ማዛወሪያ ክፍያዎችንና ሌሎች ሕጋዊ ወጪዎችን ይሸፍናል፡፡
  7. ባንኩ ባለው የብድር ፖሊሲ መሠረት መስፈርቱን ለሚያሟሉ አሸናፊዎች በከፊል ብድር ሊያመቻች ይችላል።
  8. ንብረቱን መጎብኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጋምቤላ ዲስትሪክት ጋር በመነጋገር መጎብኘት ይችላሉ።
  9. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር +251475512577/+251475512588 /+25147151 82 84 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
  10. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ጋምቤላ ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-22
  • Bid closing time: 16:30
  • Bid opening: 2026-07-22 16:30
  • Region: Gambela
  • Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
  • Buyer address: DBE Head Office, Property and Facility Management Directorate Procurement Team, Tower II,5th floor,
  • Bid bond: 25%
  • Published: Jun 22, 2026
  • Posted at: 2026-06-23T09:52:45.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders