የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች እና የሠራተኞች የመዝናኛ ክበብ የካፍቴሪያ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 07/2018

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሎት- 01 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች ሎት-02 የሠራተኞች የመዝናኛ ክበብ የካፍቴሪያ አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

ጨረታውን ለመጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች በተገለፀው መስፈርት መሰረት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።

1. ተጫራቾች በዚህ ጨረታ ማስታወቂያ የተጠቀሰውን ግዥ ለማቅረብ ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸው፣ በጨረታ ለማሳተፍ የሚያበቃ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው

2. ማንኛውም ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን በባንክ የተመሰከረ /CPO/ ለሎት1 ብር 20,000.00 (ሀያ ሺህ ብር ብቻ ) ለሎት 02, ብር 50,000.00 /ሀምሳ ሺህ ብር/ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣

3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከፋይናንስ ዳይሬክቶሬት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 102 በመቅረብ ሰነዱን መግዛትና የማይመለስ ብር 300 /ሦስት መቶ ብር ብቻ/ በመከፈል ከቢሮአችን ቢሮ ቁጥር 101 በመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ሰነዱን በሶፍት ኮፒ ፣ በፍላሽ ወይም በኢሜል መውሰድ ይችላሉ፣

4. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አሟልቶ ለሁለቱም ሎቶች ቴከኒካል እና ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ ፖስታ ብሎ በመለየት በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ዘወትር ከጧቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ በመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለበት፣

5. ጨረታው በአየር ላይ ከዋለ በ11ኛው ቀን በ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ ከረፋዱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮው ቁጥር 101 ይከፈታል። ሆኖም ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ይከፈታል፣

6. የጨረታው አሸናፊ እንደታወቀ ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ገንዘብ ለተሸናፊዎች ከ 7 ቀናት በኋላ ይመለሳል፣

7. የጨረታው አሸናፊ በተጫራቾች መመሪያ በተጠቀሰው መሰረት የጨረታ አሸናፊነቱ በፅሁፍ በተገለፀ ከ7/ሰባት/ ቀናት በኋላ እስከ 15 ቀናት ውስጥ አስፈላጊውን የውል ማስከበሪያ ገንዘብ በማስያዝ ወዲያውኑ ወደ የመንግስት ግዥ ዳይሬክቶሬቱ መጥቶ ውል መፈረም አለበት። ይህ ባይፈፅም የጨረታ አሸናፊነቱን በመሰረዝ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።

8. አሸናፊው ድርጅት ውል ከፈፀመ በኋላ በውሉ መሰረት በሚሰጠው ትእዛዝ መሰረት እቃዎቹን በማቅረብ ለቢሮ ንብረት ከፍል ገቢ ማድረግ አለበት፣

9. ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ

አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ

በስልክ ቁጥር 011 122 6455

አድራሻ 6 ኪሎ ወደ ጃንሜዳ መንገድ ኦሮሚያ ፍ/ቤት ፊት ለፊት

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-03
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid closing (note): ጨረታው በአየር ላይ ከዋለ በ11ኛው ቀን በ 4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-03 10:30
  • Bid opening (note): ጨረታው በአየር ላይ ከዋለ በ11ኛው ቀን ከረፋዱ በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Addis Ababa City Administration Education Bureau
  • Buyer address: 6 ኪሎ ወደ ጃንሜዳ መንገድ
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Jun 22, 2026
  • Posted at: 2026-06-23T09:54:27.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders