የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የስራ ቦታዎችን እና ቢሮዎችን የአረንጓዴ ስፍራ ስታንደርድ ባስጠበቀ መልኩ ለአገልግሎት ምቹ እና ለሰራተኞች ጤናማ አካባቢን ከመፍጠር አኳያ የገጸ-ምድር ማስዋብ ስራዎችን እና የአረንጋዴ ስፍራዎችን መንከባከብ አገልግሎት ግዥ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ኢኤአ/ፍፋግ/ ግጩ-038/2018
ተቋማችን የስራ ቦታዎችን እና ቢሮዎችን የአረንጓዴ ስፍራ ስታንደርድ ባስጠበቀ መልኩ ለአገልግሎት ምቹ እና ለሰራተኞች ጤናማ አካባቢን ከመፍጠር አኳያ የገጸ-ምድር ማስዋብ ስራዎችን እና የአረንጋዴ ስፍራዎችን መንከባከብ አገልግሎት ግዥ በዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
|
ሎት |
የዕቃው ዓይነት |
የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO) |
የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
|
1 |
የአረንጓዴ ስፍራዎች የመንከባከብ እና ማስዋብ ስራ አገልግሎት ግዥ |
30,000.00 |
ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት |
ሰኔ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት |
1. ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑ ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ፣ የታደሰ የታክስ ከሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
2. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ሜከሲኮ ንብ ባንክ በሚገኝበት ዋናው መስሪያቤት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 10ኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው ፍሊትና ፋሲሊቲ ግዥ ክፍል በመምጣት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000068699332 በመክፈል ሶፍት ኮፒ በኢሜይል አድራሻቸው መውሰድ ይችላሉ።
3. አድራሻ፡- ሜክሲኮ ንብ ባንክ በሚገኝበት ዋናው መስሪያ ቤት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋናው መስሪያ ቤት 10ኛ ፎቅ ላይ ፍሊትና ፋሲሊቲ ግዥ ከፍል ስልክ ቁጥር 011-156-01-48
4. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና <ETHIOPIAN ELECTRIC UTILITY> በሚል መሆን ይኖርበታል፤
5. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ከላይ እስከ ተጠቀሰው ቀን፣ሰዓት እና አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣
6, ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
7. ተቋሙ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
Tender details
- Deadline: 2026-07-07
- Bid closing time: 14:00
- Bid opening: 2026-07-07 14:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Electric Utility
- Bid bond: 30,000.00 ብር
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: Jun 23, 2026
- Posted at: 2026-06-23T10:19:51.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.