የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ የሚገኝ ሲሆን ፋብሪካው Black Master Batch ብዛት 33 ቶን እና Yellow Master Batch ብዛት 300 ኪሎ ግራም በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የብሔራዊ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር APF/25/2018/Local
የአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ የሚገኝ ሲሆን ፋብሪካው
- ሎት 1 Black Master Batch ብዛት 33 ቶን እና
- ሎት 2 Yellow Master Batch ብዛት 300 ኪሎግራም በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የጥሬ እቃዎች የማቅረቢያ ቦታ ባህርዳር እስከ ፋብሪካው የመሥሪያ ቦታ ድረስ ሲሆን በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
1. ለ2018 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት እና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ቅጅ (Copy) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በፋብሪካው የፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 105 በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
3. በአማራ ፓይፕ ፋብሪካ ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባህር ዳር ቅርንጫፍ በተከፈተው የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000013149996 ገንዘቡን ገቢ በማድረግ የባንክ ደረሰኙን በኢ-ሜይል አድራሻችን amharapipefactory@gmail.com በመላክ የጨረታ ሠነዱን ሶፍት ኮፒ በኢ- ሜይል በማግኘት በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
4. ተወዳዳሪ ድርጅቶች ለተወዳደሩበት ሎት ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲ.ፒ.ኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በፋብሪካው ስም በማሰራት የጨረታ ማስከበሪያ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ሆኖም ግን የጨረታ ማስከበሪያው ከብር 500,000.00 አይበልጥም።
5. ተጫራቾች የሕጋዊነት ማረጋገጫ ሰነዶችን ኮፒ እና የጥሬ ዕቃዎችን ዝርዝር የቴከኒክ መስፈርት በአንድ ላይ የቴክኒክ የመጫረቻ ሠነድ (Technical Bid Offer) በማለት ለብቻው በፖስታ በማሸግ እና ዋና ወይም ቅጂ ብሎ በጽሑፍ በመለየት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ዋጋቸውን እና የጨረታ ማስከበሪያቸውን ለብቻው በፖስታ በማሸግ የፋይናንሻል የመጫረቻ ሠነድ (Financial Bid Offer) በማለት ዋና ወይም ቅጂ ብሎ በጽሑፍ በመለየት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. በእያንዳንዱ ሎት ውስጥ ለተዘረዘሩት ጥሬ ዕቃዎች ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረበው ተጫራች የውድድሩ አሸናፊ ይሆናል።
8. የውድድሩ አሸናፊ ተጫራቾች ጥሬ እቃዎችን የሚያቀርቡበትን ቀናት በግልጽ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡ ይሁን እንጂ የማቅረቢያ ጊዜው አሸናፊነቱ ከተገለፀበት ዕለት ጀምሮ በሚቆጠር በ20 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማቅረብ አለበት።
9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ15ኛው ቀን ቢሮ ቁጥር 206 ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 8፡30 ይከፈታል።
10. 15ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የሕዝብ በዓል ቀን ከሆነ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
11. ፋብሪካው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 206 በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 09-35-98-37-29 / 09-18-70-18-26 መደወል ይችላሉ።
ባህር ዳር
አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ
Tender details
- Deadline: 2026-07-07
- Bid closing time: 14:00
- Bid closing (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-07-07 14:30
- Bid opening (note): ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት
- Region: Amhara
- Publishing entity: Amhara Pipe Factory PLC
- Buyer TIN: 0006196550
- Bid bond: 2% ሆኖም ግን የጨረታ ማስከበሪያው ከብር 500,000.00 አይበልጥም፡፡
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: Jun 23, 2026
- Posted at: 2026-06-23T10:39:34.000Z
- Buyer website: https://amharapipe.et/
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.