ዋን ኤከር ፈንድ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ጥራት ያለው የዘይቱን ዘር በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የዘይቱን ዘር የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ
ዋን ኤከር ፈንድ ኢትዮጵያ ከፍተኛ ጥራት ያለው የዘይቱን ዘር በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ይህንን ዘር ችግኞችን ለማፍላት ጥቅም ላይ የሚዉል ሲሆን፣ ችግኞችን ለአርሶ አደሮች በማከፋፈል (በማሰራጨት)፣ አርሶ አደሮቹ ዛፎችን በማልማት ሀብታቸውን እንዲጨምሩ፣ ገቢያቸውን እንዲያሰፉ እና አካባቢያቸውን እንዲያለሙ (እንዲያሻሽሉ) ይደረጋል።
- የሚያስፈልገው የዘይቱን ዘር መጠን 2,764,251 ዘሮች ሲሆን፣ ይህም በአንድ ኪሎ ግራም 85,000 ዘሮች እንዳሉ በመገመት 32.5 ኪ.ግ ዘር ይፈለጋል ። ይህ ደግሞ በግምት 498 ኪ.ግ የዘይቱን ፍሬ ከሚገኝ ዘር ሊሰበሰብ ይችላል። ይህ መጠን ውል ከመፈረሙ በፊት ሊቀየር ይችላል፡
- ጨረታ አቅራቢዎች ዘሩን ከፍራፍሬው የመለየት እናየማዘጋጀት ኃላፊነት ይጠበቅባቸዋል።
- አንድ ጨረታ አቅራቢ ዘር ለመሸጥ ካልቻለ/ካልፈለገ እና ፍራፍሬውን ብቻ ለመሸጥ ከፈለገ፣ አሁንም ጨረታውን ማቅረብ ይችላል፣ ነገር ግን ተመራጭነቱ ይቀንሳል፡፡
- ተጫራቹ የእናት ዛፍ ምርጫን፣ የዘር አሰባሰብ ሂደትን እና ዘሩን ከፍራፍሬው የመለይት ሂደትን ባለሙያ እንዲከታተል እና አቅጣጫ እንዲሰጥ ፈቃደኛ መሆን አለበት።
- የዘር ዝግጅት በጥላ ስር ማድረቅን እና ከዚያም በአመድ መቀባትን ያካትታል። የመጨረሻው የዘይቱን ዘር እርጥበት መጠን 8% - 10% መሆን አለበት።
- 2 የዋጋ አሰጣጥ አማራጮች አሉ። ወይ ተጫራቹ ሙሉ ለሙሉ ለተመረተ ዘር በኪሎ ግራም የመጨረሻውን ዋጋ ይሰጣል ወይም ፍሬውን ለማቀነባበር ከሚመጣው ዋጋ ጋር በኪሎ ግራም ይሰጣል።
- ለጥራት ሲባል የዘይቱን ዘር ፍሬዎች ከባህርዳር ከተማ አንዳሳ ቀበሌ ቢሆን ይመከራል።
ጨረታውን ለማቅረብ የሚፈልጉ ፈቃድ ያላቸው የዘር ሻጮች፣ እባክዎን የሚከተለውን የዋጋ ቅጠል ሞልተው፣ ፈርመው እና አትመው ወደዚህ ይላኩ፦
- ኢሜይል ethiopia.bidsubmissions@oneacrefund.org
- ማሳሰቢያ፡ ማንኛውንም የዋን አከር ፈንድ ሰራተኛ ጉቦ ለመስጠት መሞከር ከድርጅቱ ጋር እስከመጨረሻው መታገድን ያስከትላል።
- የጨረታው የመጨረሻ ቀን ሰኔ 30, 2026
- ለተጨማሪ መረጃ እና ማናቸውም ጥያቄዎች፣ እባክዎን በዚህ ይደውሉ፡ +251 98 478 4748
የዘይቱን ዘር ጨረታ ቅጽ
|
ጥያቄ |
መልስ |
|
ዋጋ በአንድ ኪሎ ግራም የዘይቱን ዘር የተዘጋጀ |
|
|
ለዘር ዋጋ በኪ.ግ መስጠት ካልቻሉ፣ የፍሬው ዋጋ በኪ.ግ ስንት ነው? |
|
|
ለዘር ዋጋ በኪ.ግ መስጠት ካልቻሉ፣ ከ498 ኪ.ግ የዘይቱን ፍሬ ዘርን ለማውጣትና ለማዘጋጀት የሚያስፈልገው ዋጋ ስንት ነው? |
|
|
ሊያቀርቡ የሚችሉት የዘይቱን ዘሮች አጠቃላይ ክብደት (ኪ.ግ) ስንት ነው? |
|
|
ዛፎቹ የሚገኙት የት ነው (ቀበሌና ወረዳ)? |
|
|
ባለሙያ የምርጫ፣ የመሰብሰብ እና የማውጣት ሂደትን ተመልክቶ እንዲመራው ለመፍቀድ ፈቃደኛ ነዎት? |
|
|
ውሉ ከተፈረመ በኋላ 32.5 ኪ.ግ ዘር ሙሉ በሙሉ ለመሰብሰብ፣ ለማውጣትና ለማዘጋጀት ምን ያህል ጊዜ ይወስዳል (በአጭር ጊዜ ቢሆን ይመረጣል)? |
|
|
መሰብሰብ የሚጀመረው መቼ ነው? |
|
|
የንግድ ፈቃድ እና የቲን ሰርተፍኬት ማቅረብ ይችላሉ? |
|
- ዋን ኤከር ፈንድ ከማንኛውም አቅራቢ ያገኘውን ምርጥ ዋጋ ለሁሉም ተጫራቾች የማጋራት መብት አለው ።
- ዋን ኤከር ፈንድ በማንኛውም ምክንያት ማንኛውንም አቅራቢ የመቀበል ወይም ውድቅ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ዋን ኤከር ፈንድ ውሉ ከመፈረሙ በፊት በማንኛውም ጊዜ ይህንን ጨረታ ሙሉ በሙሉ ሊሰርዝ ይችላል።
- ዋን ኤከር ፈንድ ለተለያዩ አቅራቢዎች የተለያየ መጠን ሊመድብ ይችላል ። እንዲሁም የተሰጠውን መጠን ከመግዛት ሊቆጠብ ይችላል ። መጠኖቹ የመጨረሻ አይደሉም፣ እና የመጨረሻ ውል ከመፈረሙ በፊት ሊቀየሩ ይችላሉ ።
- ዋን ኤከር ፈንድ ጨረታውን ወይም የጨረታውን ማንኛውንም ገጽታ የማሻሻል እና በማንኛውም አቅራቢ የቀረበውን ጨረታ በማንኛውም ምክንያት፥ ለዚያ ውሳኔ እና እርምጃ ምክንያት ማቅረብ ሳያስፈልገው ውድቅ የማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው ።
Tender details
- Deadline: 2026-07-07
- Bid closing time: 17:00
- Bid opening: 2026-07-07 17:00
- Bid opening (note): የጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለጸም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: One Acre Fund
- Buyer TIN: 0041750397
- Buyer address: Yeka Sub City, Woreda 8, Level 5, Building Opposite Misrak Polytechnic College, Addis Ababa, Ethiopia Or Kebele 13, Bahir Dar, Amhara Region(Bahir Dar office)
- Published: Jun 23, 2026
- Posted at: 2026-06-23T14:19:01.000Z
- Buyer website: https://oneacrefund.org/
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.