በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ቴሌቪዥኖችን በሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ በኦንላይን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
ኦንላይን የሐራጅ ጨረታ ቁጥር AE02/2018

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎች ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ በኦንላይን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት፡-

ኦንላይን የሐራጅ ጨረታ ቁጥር AE02/2018 በ22/10/2018 የተለያዩ ቴሌቪዥኖችን በኦንላይን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች

1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑ ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሠጠ ማስረጃ እና መለያ ቁጥሩን በኦንላይን ማቅረብ የሚችል መሆን ይጠበቅበታል።

2. በኦንላይን የሐራጅ ጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች የሚገኙት በድሬዳዋ ሙድአነኖ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የውርስ ዕቃ መጋዘን ውስጥ ነው።

3. ኦንላይን የሐራጅ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ማስታወቂያ ላይ በተጠቀሰው ቀን መሰረት በኦንላይን ብር 100 በመግዛት ጨረታ ላይ መሳተፍ ይቻላል:: የዕቃዎችን ሳንፕል በኦንላይን ማግኘት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ እቃዎቹን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር የቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።

4. ጨረታው የሚካሄደው በኦንላይን ነው።

5. በኦንላይን የሐራጅ ጨረታ ለሽያጭ የቀረቡት እቃዎች በኮድ የተከፋፈለ ሲሆን ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት።

6. ተጫራቾች በኦንላይን የሐራጅ ጨረታ ለመጫረት ለእያንዳነዱ ኮዶች የተቀመጠውን ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ዋጋ 5% በ(Tele birr) Auction Ethiopia ወይንም በባንክ (ንግድ ባንክ) የተረጋገጠ (CPO) በድሬዳዋ ጉምሩከ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል።

7. ተጫራቾች በኦንላይን ሐራጅ ጨረታ ኦንላይን ከሆነበት ከ17/10/2018 4:00 ጀምሮ እስከ ጨረታው የሚከፈትበት ቀን 22/10/2018 4:00 ሰዓት መሳተፍ ይጠበቅባቸዋል።

8. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ተጫራች በጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒኦ በሶፍት ኮፒ የተሰራ ከሆነ በሶስት የስራ ቀናቶች ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

9. አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን እቃዎች አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበት ገንዘብ ገቢ በማድግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል።

10. ከላይ በተራ ቁጥር 9 ላይ በተገለጹ ቀናቶች ውስጥ ክፍያውን ፈጽሞ ዕቃውን ያልተረከበ በተጫራች በጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ለባለስልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ የሚቀረብ መሆኑን እንገልፃለን።

11. የጉምሩክ ኮምሽን ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0915 460 970 (0912 885 746) መደወል ይቻላል
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-06-29
  • Publishing entity: Ministry of Customs Diredawa Branch Bureau
  • Bid bond: 5% ለእያንዳነዱ ኮዶች
  • Bid document price: 100 (አንድ መቶ ብር)
  • Published: Jun 24, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders