Disposal, scrap and surplus sales
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎችን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የሐራጅ ጨረታ ቁጥር 0016/2018
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኝ የተለያዩ ዕቃዎችን ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት፡-
በሐራጅ ጨረታ ቁጥር 0016/18 በ24/10/2018
- የተለያዩ አልባሳት፣
- ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች፣
- ጫማዎች፣
- የቤት እና
- የቢሮ ዕቃዎች እና
- ማስዋቢያዎች፣
- የሞባይል ግላሶች እና ከቨሮች፣
- የእጅ ሰዓቶች፣
- ስፔርፓርቶች፣
- የእይታ ዕቃዎች መነፅሮች፣
- የመሬት ምንጣፍ፣
- ኮስሞቲክስ እና
- መዋቢያዎች እና
- የንፅህና መጠበቂያዎች፣
- የስፖርት ዕቃዎች፣
- የተለያዩ አርትፊሻል ጌጣጌጥ እና ሌሎች የተለያዩ ዕቃዎች ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሽጥ ይፈልጋል።
ስለዚህ በጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች፣
- የታደሰ በዘርፉ የፀና የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መሥሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ እና መለያ ቁጥሩን ማቅረብ የሚችል መሆን ይጠበቅበታል።
- ለጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎች የሚገኙት በድሬዳዋ ሙድአነኖ ግቢ ውስጥ በሚገኘው የውርስ ዕቃ መጋዘን ውስጥ ነው፡
- በሐራጅ ጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ሰነድ ድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ገቢ አሰባሰብ እና ዋስትና አያያዝ ቡድን ገንዘብ ያዥ ቢሮ በመቅረብ ብር 100 በመክፈል በመግዛት ከ17/10/2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 1:30 እስከ 6፡00 ከሰዓት ከ8:30 ሰዓት እስከ ቀኑ 12፡00 ሰአት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ንብረቱ በሚገኝበት መጋዘን በመቅረብ ማየት ይቻላል። ነገር ግን እቃዎቹን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር የቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።
- ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ በድሬዳዋ ሙድአነኖ ግቢ ነው።
- ለሐራጅ ጨረታ ለሽያጭ የቀረቡት እቃዎች በኮድ የተከፋፈለ ሲሆን ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት መሆን አለበት።
- ተጫራቾች በሐራጅ ጨረታ ለመጫረት ለኮዱ የተቀመጠ 5% ለጨረታው ዋስትና ማስከበረያ (CPO) በባንክ (ንግድ ባንክ) የተረጋገጠ በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሠራት ይኖርባቸዋል።
- በሐራጅ ጨረታ ለወጡት ለእያንዳንዱ ኮዶች በጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ (CPO በባንክ (ንግድ ባንክ) የተረጋገጠ በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሠራት ይኖርባቸዋል።
- የሐራጅ ጨረታ ለሚካሄደው በማስታወቂያ መሰረት በዕለቱ ጠዋት በ2፡00 ሰዓት ምዝገባ ጀምረን እንደተጠናቀቀ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ጨረታው ይጀምራል።
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፈለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒኦ በሶስት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደሩበትን ዕቃዎች አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ንብረቱን መረከብ ይኖርበታል።
- ከላይ በተራ ቁጥር 10 ላይ በተገለፁት ቀናቶች ውስጥ ክፍያውን ፈጽሞ ዕቃውን ያልተረከበ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ሲፒኦ ለባለሥልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለጨረታ ይቀርባል።
- የጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 15 46 09 70 (09 12 88 57 46) መደወል ይቻላል።
በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-07-01
- Bid closing time: 10:30
- Bid opening: 2026-07-01 10:30
- Region: Dire Dawa
- Publishing entity: Ministry of Customs Diredawa Branch Bureau
- Bid bond: 5%
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published on: Addis Zemen (Jun 24, 2026)
- Posted at: 2026-06-24T07:35:51.000Z