በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ተሽከርካሪዎች እና ባለሶስት እግር ተሽከርካሪዎች በሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ

የሐራጅ ጨረታ ቁጥር 005/2018

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት ውርስ ሆኖ በመጋዘን የሚገኙ

  • ተሽከርካሪዎች እና ባለሶስት እግር ተሸከርካሪዎች

ይህ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሐራጅ ጨረታ ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚሁ መሰረት፡-

በሐራጅ ጨረታ ቁጥር 005/2018 በ24/10/2018 ዓ.ም ባለበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ ለጨረታ የቀረቡትን ተሸከርካሪዎች ለመጫረት የሚፈልግ ተጫራች

  1. ማንኛውም ዕድሜው ከ18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ የታደሰ መታወቂያ ወይም የኢትዮጵያ ዲጂታል መታወቂያ ካርድ ያለው/ያላት
  2. ለጨረታ የቀረቡት ተሸከርካሪዎች ሲሆን የሚገኘው ድሬዳዋ ሙዲአነኖ ግቢ በሚገኘው ተሽከርካሪ መጋዘን ውስጥ ነው።
  3. የተሽከረካሪው አስመጪ ወይም ባለቤትና ቤተሰብ የሆነ ሰው በጨረታ መሳተፍ አይችልም።
  4. በጨረታው ሰነድ ላይ በተገለጸው መስፈርት መሰረት በመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ገቢ አሰባሰብ እና ዋስትና አያያዝ ቡድን ገንዘብ ያዥ ቢሮ ከ17/10/2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 1፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት 8፡30 እስከ ቀኑ 12፡00 ሰአት እንዲሁም ቅዳሜ ከ2፡00 ሰአት እስከ 6፡00 ሰአት ድረስ በመቅረብ ብር 100 በመክፈል ሰነዱን በመግዛት ተሽከርካሪው በሚገኝበት መጋዘን በመቅረብ ማየት ይቻላል።
  5. ተሽከርካረውን ሳያዩ ዋጋ ሰጥቶ ለሚፈጠረው ችግር የቅ/ጽ/ቤቱ ተጠያቂ አይሆንም።
  6. ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ ድሬዳዋ ሙዲአነኖ የሚገኘው ግቢ ውስጥ ነው።
  7. ተጫራቾች ለተሸከርካሪው የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊት ያለውን ዋጋ መሆን አለበት።
  8. ተጫራቾች ተሽከርካሪውን በመግዛት በጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ በንግድ ባንክ የተረጋገጠ(CPO) በድሬዳዋ ጉምሩክ ኮሚሽን ቅ/ጽ/ቤት ስም ማሠራት ይኖርባቸዋል።
  9. የሐራጅ ጨረታ የሚካሄደው በማስታወቂያ መሰረት በዕለቱ ጠዋት በ2፡00 ሰዓት ምዝገባ ጀምረን እንደተጠናቀቀ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ ጨረታው ይጀምራል።
  10. በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች በጨረታ ዋስትና ያስያዘው ሲፒኦ ከሚከፍለው ዋጋ ጋር የሚታሰብ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ ሲፒኦ በሶስት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ተመላሽ ይደረግባቸዋል።
  11. የጨረታ አሸናፊ የሆነ ተጫራች የተወዳደረበትን ተሽከርካሪ አሸናፊ ስለመሆኑ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናቶች ውስጥ ያሸነፈበት ገንዘብ ገቢ በማድረግ ተሽከርካሪውን መረከብ ይኖርበታል።
  12. ከላይ በተራ ቁጥር 11 ላይ በተገለጸው ቀናቶች ውስጥ ክፍያውን ፈጽሞ ተሽከርካሪውን ያልተረከበ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘውን ሲፒኦ ለባለሥልጣኑ መ/ቤት ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ በጨረታ ይቀርባል።
  13. የጉምሩክ ኮሚሽን ድ/ዳ/ቅ/ጽ/ቤት ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 09 15 46 09 70 (09 12 88 57 46) መደወል ይቻላል።

በጉምሩክ ኮሚሽን የድሬዳዋ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-01
  • Publishing entity: Ministry of Customs Diredawa Branch Bureau
  • Bid document price: 100.00 ብር
  • Published: Jun 24, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders