የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ጫማዎች፣ አልባሳት፣ ኮስሞቲክስ፣ የመኪና መለዋወጫ፣ ኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ተሽከርካሪ መኪናዎች፣ የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ፣ ምግብ ነክ፣ እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩከ ሕግን ተላልፈው የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በቀን 24/10/2018 ዓ/ም እና 27/10/2018 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት መግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሥም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት በተጫራች ስም የማይመለስ 100 (መቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየትና እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በሟሟላት በጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት፡ ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣልዎት የምትፈልጉት የዕቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልክ ቁጥር 022-224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት እንዲመጣልዎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

የጨረታ መስፈርቶች፡-

1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክሰ ምዝገባ ሰርትፍኬት፣የዘመኑን ግብር የከፈለ ሰለ መሆኑ ክሊራንሰ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክሰ እንቅሰቃሴያቸውን ለታክሰ ማዕከሉ ያሳወቁበት፣በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምሰክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል።

2. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዘውትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን 24/10/2018 ዓ/ም እና 27/10/2018 ባሉት ቀናት ለግልፅ እስከ ጠዋቱ 3፡45 እንዲሁም ለሐራጅ ጨረታ በዚሁ ቀን እስከ ረፋዱ 5፡00 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት በመግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይችላሉ።

3. ለግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (cpo) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5% እንዲሁም ለሃራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4. ተጨራቾች በሚከተለው የጨረታ ቀናት (እሰኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ።

የጨረታ ቦታ

የጨረታ ዓይነት

ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች

የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ

የጨረታዉ የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

 

ቃሊቲ ጉምሩክ

ግልጽ እና ሐራጅ

ጫማዎች፣ አልባሳት፣ ኮስሞቲክስ፣ የመኪና መለዋወጫ፣ ኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ተሽከርካሪ መኪናዎች፣ የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ፣ ምግብነክ፣ እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች

ለግልፅ ጨረታ እስከ 24/10/2018 እሮብ እና ዓርብ ቅዳሜ ጠዋቱ 345 እና ለሃራጅ ጨረታ እስከ 445

ለግልፅ ጨረታ በ24/10/18 እና 27/10/2018 ጠዋቱ 345 እና ለሃራጅ ጨረታ እስከ 500

5. የጨረታው መከፈቻ ቦታ በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።

6. ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታዉ ዋሰትና ያስያዙት (C.P.O) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸዉ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ዉጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ 3 የሰራ ቀናት ውሰጥ ተመላሸ ይደረግላቸዋል።

7. ከአሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸዉ በደብዳቤ ከተገለጸላቸዉ ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ዉሰጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዉን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖርበታል።

8. ከላይ በተ.ቁ.7 በተገለጹት ቀናት ውሰጥ ክፍያዉን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበው ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታው መስረከቢያ ያስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋ ለኮሚሸኑ ገቢ ሆኖ ዕቃዉ በድጋሜ ለሸያጭ ይቀርባል።

9. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።

  • ለተጨማሪ መረጃ በሰልክ ቁጥር፡- 022-224-1402 ደውለው ስለጨረታው መረጃ መጠየቅ ይቻላል።

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-04
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የጨረታው ቀን እና ሰዓት ይለያያል
  • Bid opening: 2026-07-04 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታው ቀን እና ሰዓት ይለያያል
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Awash Custom Commission Branch Office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
  • Published: Jun 24, 2026
  • Posted at: 2026-06-24T07:53:08.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders