በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መ/ጣቢዎች ተይዘው እና ተወርሰው የሚገኙ ዕቃዎች በግልጽ እና በሃራጅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 39/2018

በኢትዮጵያ ጉምሩከ ኮሚሽን የሞያሌ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በቅ/ጽ/ቤቱ እና በስሩ የሚገኙ መ/ጣቢዎች ተይዞው እና ተወርሰው የሚገኙ ተሸከርካሪዎች፣ የሞተርሳይክል እና የተሸከርካሪ መለዋወጫዎች አልባሳት፤ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ የመገናኛ መሳሪያዎች፣ ኮስሞቲክስ እና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች፣ የቤት ውስጥ መገልገያ እና ማስዋቢያ ዕቃዎች፣ ምግብ ነከ ዕቃዎች እና ተሽከሪካሪ መኪና እንዲሁም ሌሎች ዕቃዎች በግልጽ እና በሃራጅ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመሽጥ ይፈልጋል። በዚህ መሠረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጨረታ ቅድመ ሁኔታዎች እና መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

1. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመወዳደር የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ከሚሸጠው ዕቃዎች ጋር ተዛማችነት ያለው የታደሰ የንግድ ፊቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት፣ የዘመኑን ግብር የከፈለ ሰለመሆኑ ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታከስ እንቅስቃሴያቸውን ያሳወቁበት በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸው የምስክር ወረቀት እና መለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ በኤንቨሎፕ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።

2. ተጫራቾች የግልጽ ጨረታ ሰነድ ዘውትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00 – 12፡00 ሰዓት እና ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00 – 6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል በጽ/ቤታችን የእለት ገቢ ገንዘብ ሰብሳቢ ቢሮ ቁር 16 በመገኘት ይህ የጨረታ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ መዝጊያው ቀን ድረስ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።

3. በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) ዋስትና (CPO) እንዲሁም በሃራጅ ጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎችንም በተመለከተ ማስያዝ ያለባችሁ የሲ.ፒ.ኦ መጠን በየኮዱ የሚለያይ ስለሆነ ከጨረታ ደንብ ላይ መመልከት የምትችሉ መሆኑን እየገለጽን በጉምሩክ ኮሚሽን በሞያሌ ቅርንጫፍ ስም በባንክ የተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4. ጨረታው ሚካሄደው በሞያሌ ቅ/ጽ/ቤት ሲሆን ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) ባሉበት ወይም ታዛቢ ፊት ይከፈታል።

5.ተጫራቾች ማስታወቂያ በጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር እሰከ 7ተኛው ቀን ድረስ ለጨረታ የቀረቡ ዕቃዎች ናሙና በሞያሌ እና በሁሉም መጣቢያ የሚገኙ መጋዝኖቻችን እየሄዱ መመልከት አለባቸው።

6. ጨረታው የሚካሄደው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀሚሮ የሚቆጠር በ8ኛው ቀን ሲሆን ጨረታው ከጠዋቱ 3፡45 (ሶስት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ) ተዝግቶ 4፡00 (አራት ሰዓት) ላይ ይከፈታል

7. ከላይ በተራ ቁጥር 6 በተገለጸው ጋዜጣው ከታተመበት ቀን ጀሚሮ የምቆጠር 8ኛው ቀን የስራ ቀን ሳይሆን ከቀረ ጨረታው መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።

8.ለጨረታው አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታው ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ (C.PO) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸው ሲሆን ለተሸናፍ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታውን ውጤት ከተገለጸ በ 3 ቀናት ውሰጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

9. አሸናፊ ተጫራች ማሸነፋቸውን በደብዳቤ ወይም በማስታወቂያ ከተገለጸላቸው ቀን ጀሚሮ በ5 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃውን መረከብ ይኖርባቸዋል።

10. ከላይ በተራ ቁጥር 9 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ክፍያውን ገቢ ያላደረገ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት CPO ለመ/ቤቱ ገቢ ሆኖ ዕቃው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

11. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 046 444 1415/046 444 1564 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።

በኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የሞያሌ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-01
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀሚሮ የሚቆጠር በ8ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡45 (ሶስት ሰዓት ከአርባ አምስት ደቂቃ)
  • Bid opening: 2026-07-01 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀሚሮ የሚቆጠር በ8ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 (አራት ሰዓት)
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Moyale Customs Branch Office
  • Bid bond: በግልፅ ጨረታው 5% እንዲሁም በሃራጅ ጨረታ የሚቀርቡ ዕቃዎችንም በተመለከተ በየኮዱ የሚለያይ ይሆናል
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
  • Published: Jun 24, 2026
  • Posted at: 2026-06-24T07:57:52.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders