የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለሚያከናወነው አስቸኳይ ፕሮጀክቶች ግብዓት የሚያገለግል የኮንክሪት ሚክስ ምርት በቁርጥ ዋጋ መግዛት ይፈልጋል
Description
የኮንክሪት ሚክስ የቁርጥ ዋጋ
ግዥ ጥሪ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ለሚያከናውነው አስቸኳይ ፕሮጀክቶች ግብዓት የሚያገለግል የኮንከሪት ሚክስ ምርት በቁርጥ ዋጋ ከዚህ በታች የተቀመጡትን መስፈርቶች ከሚያሟሉ አቅራቢዎች መግዛት ይፈልጋል።
|
|
የምርቱ ዓይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
የአንድ ሜ.ኩ. ነጠላ ዋጋ ትራንስፖርት ተ.እ.ታ ጨምሮ |
|
1 |
Concrete C-25 With out Pump |
ሜ.ኩ |
3,372 |
18,105.03 |
|
2 |
Concrete C-30 With out Pump |
ሜ.ኩ |
165 |
18,735.03 |
|
3 |
Concrete C-30 With Pump |
ሜ.ኩ |
1,500 |
19,285.03 |
1. አግባነት ያለው የዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ታክስ ክሊራንስ ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ እንዲሁም በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ ገጽ ላይ መመዝገብ ይኖርባቸዋል።
2. የኮንክሪት ሚከስ ማምረቻ ማሽን የባለቤትነት ማረጋገጫ ወይም ህጋዊ ውክልና በህግ አግባብነት ካለው አካልየተሰጠ የኮንክሪት ሚከስ ለማምረትና ለገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ፍቃድ፣ ወይም ኮንክሪት ሚክስ ለማምረትናለገበያ ለማቅረብ የሚያስችል ፍቃድ ካለው ግለሰብ/ማህበር የተሰጠ ህጋዊ/በፈዴራል ሰነዶች ማረጋገጫ ጽ/ቤት የተረጋገጠ ውክልና ኢያይዞ ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቹ ለእያንዳንዱ የኮንክሪት ምርት አይነት በቀን ቢያንስ 20 ሜ.ከ ወይም ከሶስቱም የምርት አይነቶችበድምሩ ቢያንስ በቀን 60 ሜ.ኩ እና ከዚያ በላይ ምርት የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
4. የሚቀርበው ምርት በባለስልጣን መ/ቤቱ የጥራት መመዘኛ መስፈርት /specification/ መሰረት መሆኑ መ/ቤቱ የላብራቶሪ የጥራት ፍተሻ ያከናወናል።
5. አቅራቢው የኮንክሪት አይነቶች ሚክስ ዲዛይን ዶከመንት የኮንከሪት ጠጠር እና አሸዋ የጥራት ማረጋገጫ ላብራቶሪ ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባለፉት ስድስት ወራት ጊዜ ውስጥ ፍቃድ ካለው የላብራቶሪ ማዕከል ወይም ተጫራቹ በራሱ ላብራቶሪ የተከናወነ ሆኖ ህጋዊ ስልጣን ባለው ተቋም/አማካሪ የተረጋገጠ ዶክመንት ሪፖርት ማቅረብ አለበት።
6. ተጫራቾች ቢያንስ ሲሚንቶ 500 ኩንታል ሲሚንቶ ኮንክሪት አግሪጌት 1000 ሜ.ኩ ፋይን አግሪጌት 1000 ሜ.ኩ ክምችት በሳይት ላይ ስለመኖሩ በደብዳቤ ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።
7. ተጫራቾች ኮንከሪት ማምረቻ ማሽኑን በሚመለከት የማሽኑን የማምረት አቅም የሚገልፅ ቴክኒካል ሰነድ/ሊብሬ/ ማቅረብ አለበት። የኮንክሪት ባቺንግ ፕላንቱ ዝቅተኛ የማምረት አቅሙ 30m3/Hr መሆን አለበት። ማረጋገጫ በፅሁፍ ማቅረብ አለባቸው።
8. በሀገር አቀፍ ደረጃ የነዳጅ ዋጋ ላይ በሚደረግ ማስተካከያ መሰረት ኮንከሪት ሚክስ ማጓጓዣ የትራንስፖርት ወጪ ላይ ብቻ በውል አፈፃፀም በሚፀድቅ የነዳጅ ፍጆታ ተመን መሰረት ማስተካከያ የሚደረግ ይሆናል።
9. አቅራቢዎች ለምዝገባ በሚቀርቡበት ቅደም ተከተል መሰረት የመ/ቤቱ ፍላጎት እስኪሟላ ድረስ ይስተናገዳሉ።
10. አቅራቢዎች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ወይም በሬዲዮ ጥሪ ከተላለፈበት ቀን ጀምሮ በስራ ቀን እና ሰዓት በባለስልጣኑ ዋና መ/ቤት 1ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 023 ከላይ የተገለፁትን ማስረጃዎች ኦርጅናልና ኮፒ ይዘው በመቅረብ መመዝገብ ይኖርባቸዋል።
ባለስልጣን መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ የግዥ ፍላጎቱን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ ስ.ቁ 011-3-72-28-25 / 011-3-71-41-03
የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን
Tender details
- Deadline: 2026-07-13
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
- Bid opening: 2026-07-13 12:00
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት አልተገለፀም
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Addis Ababa City Roads Authority
- Buyer address: አዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን ሳር ቤት ፑሽኪን አደባባይ ሳይደርስ
- Published: Jun 24, 2026
- Posted at: 2026-06-24T07:59:09.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.