የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለጎፋ አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ 3kg Carbon dioxide Fire extinguisher እና ለጃንሜዳ G+10 ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል Supply and Fix Satellite Dish System ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/BM/87/2026 እና DCE/SE/88/2026
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለጎፋ አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ 3kg Carbon dioxide Fire extinguisher እና ለጃንሜዳ G+10 ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል Supply and Fix Satellite dish system ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
የፕሮጀክት ስም |
የጨረታ ቁጥር |
የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
1 |
3Kg Carbon dioxide Fire extinguisher |
ጎፋ አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት |
DCE/BM/87/2026
|
ሀምሌ 01/2018 ዓ.ም 8፡15 ሰዓት |
ሀምሌ 01/2018 ዓ.ም 8፡30 ሰዓት |
100,000.00
|
|
2 |
Supply and Fix Satellite dish system |
ጃንሜዳ G+10 ግንባታ ፕሮጀክት
|
DCE/SF/88/2026
|
ሀምሌ 01/2018 ዓ.ም 8፡30 ሰዓት |
ሀምሌ 01/2018 ዓ.ም 8፡45 ሰዓት |
100,000.00
|
ስለሆነም፡-
- ተጫራቾች በዘርፍ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት (ታከስ ክሊራንስ) እና የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ… ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ በሰንጠረዥ በተገለፀው መሠረት በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ለ120 (አንድ መቶ ሃያ) Calendar days ፀንቶ የሚቆይ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ቃሊቲ ቶታል ማደያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መ.ኮ.ድ ግቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መ/ቤት የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተያያዘው ዝርዝር እና ብዛት መሠረት መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- ቃሊቲ ቶታል ማደያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መ.ኮ.ድ ገቢ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 011 440 3434
ማዞሪያ 011 442-2270/71/72 E-mail አድራሻ Info@dce-et.com
የድረ-ገፅ አድራሻ www.dce-et.com
ፖ.ሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁ.011 440-0471
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
Tender details
- Deadline: 2026-07-08
- Bid closing time: 14:30
- Bid closing (note): የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Bid opening: 2026-07-08 14:45
- Bid opening (note): የጨረታው መክፈቻ ቀንና ሰዓት የተለያየ ነው
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Defense Construction Enterprise (DCE)
- Buyer address: ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ
- Bid bond: 100,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ሎት
- Bid document price: 200.00 ብር ለእያንዳንዱ
- Published: Jun 24, 2026
- Posted at: 2026-06-24T08:26:13.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.