አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማህበር Sony Camera a7 v እና አክሰሰሪዎች በግልፅ ጨረታ መሰረት ለመግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር፡ AWACH/NCB/G/02/2018/26
አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሠረታዊ የኅብረት ሥራ ማህበር Sony Camera a7 v እና አክሰሰሪዎች በግልፅ ጨረታ ከዚህ በታች በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተወዳዳሪዎች ተጫራቾች፡-
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ከገቢዎች ሚኒስቴር በጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የታደሰ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ትብብር ሚኒስቴር የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው።
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ የምዝገባ ማስረጃ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 300/ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል አዋሬ፣ ሴቶች አደባባይ በሀብትሽ አውቶሞቲቭ ገባ ብሎ ወደ አደዋ ድልድይ በሚወስደው መንገድ ላይ አጋር ሕንጻ፣ 2ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 201 በአካል በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ።
5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዱ ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች ለሚያቀርቧቸው ካሜራና አከሰሰሪዎች በሙሉ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. በሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፣ ሙሉ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን እንዲሁም የድርጅቱን ማህተም አሟልተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8. በተጫራቾች ዋጋ ላይ ተንተርሶ የሚቀርብ ዋጋ ተቀባይነት የለውም።
9. የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣ ዕለት ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዶቻቸውን ማስገባት የሚችሉ ሲሆን በዚሁ ቀን 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል።
10. ማህበሩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 011-557-7341 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
አድራሻ፡- አዋሬ፣ ሴቶች አደባባይ በሀብትሽ አውቶሞቲቭ ገባ ብሎ አደዋ ድልድይ፣ አጋር ሕንጻ፣ 2ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 201
አዋጭ የገ/ቁ/ብ/ኃላ/የተ/መሠ/የህ/ስ/ ማህበር ዋና ቢሮ
Tender details
- Deadline: 2026-07-09
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣ ዕለት ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት
- Bid opening: 2026-07-09 12:00
- Bid opening (note): የጨረታ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣ ዕለት ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Awach Saving and Credit Cooperative Society Ltd.
- Bid bond: 100,000.00 ብር
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Jun 24, 2026
- Posted at: 2026-06-24T08:40:12.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.