በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት በከፋ ዞን የጊምቦ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 ዓ/ም በጀት ዘመን በዲሪ ቀበሌ በመለስ ዜናዊ ሁለተኛ ት/ቤት ማስፋፊያ ግንባታ ማለትም አንድ ብሎክ መማሪያ ክፍልና ሁለት ብሎክ መጸዳጃ ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግሥት በከፋ ዞን የጊምቦ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 ዓ/ም በጀት ዘመን በዲሪ ቀበሌ በመለስ ዜናዊ ሁለተኛ ት/ቤት ማስፋፊያ ግንባታ ማለትም
- አንድ ብሎክ መማሪያ ክፍልና
- ሁለት ብሎክ መጸዳጃ ቤት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት ዝርዝር መስፈርቱም
1. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉና ያሳደሱ የቲን ቁጥር እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (150,000) አንድ መቶ ሀምሳ ሺህ ብር CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
3. ተጫራቾች በGC/BC-5 ፈቃድ ያላቸው
4. ተጫራቾች CPO በጊምቦ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ሥም በማሰራት ከጨረታ ሠነድ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ሠነዱን ከፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 14 ቀርበዉ የማይመለስ ብር 1000/አንድ ሺህ ብር
6. ጨረታው ለ30 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ ውሎ በ31ኛዉ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሲሆን ታሽጎ 4:30 ሲሆን ይከፈታል።
7. ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤ ባይገኙም የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም
8. አሸናፊ ድርጅት ካሸነፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ5/አምስት/ የሥራ ቀናት ዉስጥ ውል የመግባት ግዴታ አለበት።
9. ጨረታው የሚታሸግበት ቀን ቅዳሜ፣ እሁድ ወይም ከስራ ቀን ውጭ ከሆነ በሚቀጥለዉ የስራ ቀንና ሰዓት ይሆናል።
10.መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁ/0915 178 063 / 0917 064 078 ይደውሉ
በከፋ ዞን የጊምቦ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-07-24
- Publishing entity: Gimbo Woreda Finance Bureau
- Bid bond: 150,000.00 ብር
- Bid document price: 1,000.00 ብር
- Published: Jun 24, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.