በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን የማና ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ለ2018 ዓ.ም. የበጀት ዓመት የሚያስፈልጉ የአንድ ቦታ አገልግሎት መስጫ (መሶብ)፣ የተለያዩ የቢሮ እቃዎች እና የቢሮ መጋረጃዎች መግዛት ይፈልጋል

Description

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን የማና ወረዳ ገ/ጽ/ቤት በወረዳው ለሚገኙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ለ2018 ዓ.ም የበጀት ዓመት የሚያስፈልጉ፤-

  • የአንድ ቦታ አገልግሎት መስጫ (መሶብ )
  • የተለያዩ የቢሮ እቃዎች
  • የቢሮ መጋረጃዎች

ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች እና ግዴታዎችን የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችለ መሆኑን እንገልፃለን።

የተጫራቾች መስፈርት /ግዴታዎች

1. ጥራት ያላቸውን እቃዎች ማቅረብ የሚችሉ እና በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው።

2. በመንግስት ጨረታዎች መሳተፍ የሚያሥችል የምዝገባ ምስክር ወረቀት አግባብ ካለው ሕጋዊ አካል ማቅረብ የሚችሉ።

3. የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት የግዢ ደንብ እና መመሪያ የሚያከብር።

4. የ2017 ዓ.ም ግብር የከፈሉ እና የ2018 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና ንግድ ምዝገባ ፍቃድ ያላቸው። የ2017ዓ.ም ግብር ያልከፈሉ እና ለ 2018 ንግድ ፈቃዳቸውን ካላደሱ ከሆነ ከገ/ባ/ጽ/ቤት ህጋዊ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።

5. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው።

6. የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያሳይ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል እና የመጨረሻዉን ወር የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ያወራረደበት ማስረጃ ማቅረብ የሚችል።

7. የጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ለእያንዳንዳቸው 50,000 (ሀምሳ ሺ ብር) በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ የሚችል

8. የጨረታው ዝርዝር ሰነድ የማይመለስ ብር 1000 (አንድ ሺ ብር) በመክፈል ከማ/ወ/ገ/ባ/ጽ/ቤት መግዛት የሚችል።

9. ተጫራቾች ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት የጨረታ ሰነዱን ገዝቶ ማስገባት ይቻላል።

10. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት ኦርጅናል እና ኮፒውን ለየብቻው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ሙሉ አድራሻቸውን እና የድርጅቱን ስም በመጥቀስ በ17/9/2018 ዓ.ም 4፡00 ሰአት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል። በማስታወቂያ የተነገረ የመክፈቻ ቀን የእረፍት ወይም በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል።

11. ጨረታው በተባለበት ቀን እና ሰአት ገብቶ ካለቀ በኋላ በ4:00 ሰዓት ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ 4፡30 ሰዓት በማ/ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ይከፈታል።

12. አሸናፊ ተጫራቾች ከጽ/ቤቱ ጋር ውል መፈራረም የሚችሉ እና የዉል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን ዋጋ 10% በቼክ ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት።

13. አሸናፊው የተገዙ እቃዎችን ለማና ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ንብረት ክፍል ሙሉ በሙሉ በራሱ ወጪ ማቅረብ ይኖርበታል።

14. የጨረታ ሳጥን ከታሸገ በኋላ የሚመጡ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።

15. ተጫራቾች በሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ እና የማይነበቡ ነገር ሊኖር አይገባም

16. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ነጠላ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የሚጨምር ወይም የማይጨምር መሆኑ በግልጽ ተለይቶ ሊቀመጥ ይገባል።

17. ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ፤ 047 226 0016 / 047 226 0145 ይደውሉ።

በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዞን የማና ወረዳ ገ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-24
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): በ17/9/2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-24 12:00
  • Bid opening (note): በ17/9/2018 ዓ.ም በ4፡30 ሰዓት
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Jimma Zone Mana Woreda FEDB
  • Bid bond: 50,000.00 ብር ለእያንዳንዳቸው
  • Bid document price: 1,000.00 ብር
  • Published: Jun 24, 2026
  • Posted at: 2026-06-24T09:11:51.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders