የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀድያ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር በሚገኘው የባህር ዛፍ ደን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል

Description

የባህር ዛፍ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ

Ref No: ERCS-GDS/0035/26

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀድያ ዞን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር በሚገኘው የባህር ዛፍ ደን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም ፍላጎቱ ያላቸውና እና ብቁ ተጫራቾች የታሸገ ጨረታ ሰነዶችን እንዲያቀርቡ ይጋብዛል።

ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት በጨረታው መወዳደር ይችላሉ።

1) ማንኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ በጨረታው መሳተፍ ይችላል።

2) የጨረታ ሰነዶቹን ለማግኘት ፍላጎት እና ብቃት ያላቸው ተጫራቾች የማይመለስ የጨረታ ሰነድ ክፍያ ብር 500(አምስት መቶ ብር) በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ስም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ (CBE) በተከፈተው ሂሳብ ቁጥር 1000000950487 ገቢ በማድረግ እና የባንክ ደረሰኝ በማቅረብ የጨረታ ሰነዶቹ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የሰብዓዊ ግብአት አቅርቦት መምሪያ፣ የግዥ ክፍል፣ 1ኛ ፎቅ፣ ቢሮ ቁጥር 25፣ ስታዲየም አካባቢ፣ አዲስ አበባ በመገኘት መውሰድ ይቻላል።

3) በዚህ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ማንኛውም የኢትዮጵያ ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር የሚሰራ እና ትክክለኛ የኢትዮጵያ መታወቂያ ካርድ (ID) ቅጂ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4) ሁሉም ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና (Bid Bond) በCPO ብቻ፣ ከጠቅላላ የጨረታ ዋጋ 2% መጠን ያለውን በተለየ የታሸገ ፖስታ ውስጥ ማቅረብ አለባቸው። የጨረታ ዋስትናው ከጨረታ በኋላ ለ28 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ መሆን አለበት።

5) የፋይናንስ ዋጋ ማቅረቢያ (Financial Offer) በሁለት በተለያዩ የታሸጉ ፖስታዎች ውስጥ “ዋና (Original)” እና “ቅጂ (Copy)” ተብለው በግልጽ ሁኔታ ተለይተው መቅረብ አለባቸው፡፡ የቴክኒክ ማቅረቢያ (Technical Offer) ደግሞ “ዋና የቴክኒክ ማቅረቢያ (Original Technical Offer)” ተብሎ በግልጽ ሁኔታ በተጻፈበት ሦስተኛ የታሸገ ፖስታ ውስጥ መቅረብ አለበት፡፡ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO) ተብሎ በግልጽ በተጸፈበት አራተኛ የታሸጋ ፖስታ ውስጥ መቅረብ አለበት:: አራቱም ፖስታ በአንድ ውጫዊ ፖስታ ውስጥ ተካተው መቀመጥ ያለባቸው ሲሆን፣ ውጫዊው ፖስታ በአግባቡ የታሸገ፣ ማህተም ያረፈበት እና የተፈረመ መሆን አለበት።

6) ጨረታው ሐምሌ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ የሚዘጋ ሲሆን፣ በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ዋና ጽ/ቤት በስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ውኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

7) ተጫራቾች በሆሳዕና ከተማ አስተዳደር በጀሎ ናራሞ ቀበሌ በሽለንሻ አካባቢ የሚገኝ የሀድያ ዞን ቀይ መስቀል ቅ/ጽ/ቤት የባህር ዛፍ ደን ምበቤንች ሸኮ ዞን፣ ሰሜን ቤንች ወረዳ፣ ሴሪት መንደር የሚገኘውን የባህር ዛፍ የጨረታ ሰነዶችን በጥንቃቄ እንዲመለከቱ በጥብቅ ይመከራል። የመቁረጥና የመጓጓዣ ወጪዎች ሁሉ በተጫራቹ ይሸፈናሉ።

8) የግምገማ መመዘኛዎች የቀረበውን ዋጋ፣ የተሟላ የጨረታ ዋስትና (CPO) እና በጨረታ ሰነዱ የተጠቀሱ መስፈርቶች ሁሉ መሟላትን ያካትታሉ።

9) በሌላ ሰው ስም ወይም የጨረታ ሰነድ በራሱ ስም ሳይገዛ የተሳተፈ ተጫራች ይሰረዛል።

10) አሸናፊው ተጫራች ሙሉ ክፍያ ከፈጸመ በኋላ የገዛውን ንብረት በ15 (አስር አምስት) ቀናት ውስጥ ማንሳት አለበት።

11) ተጫራቾች ከነጥብ 2 እስከ 10 የተጠቀሱትን መመሪያዎችን ካልተከተሉ ከጨረታው ውድድር ውጪ ይሆናሉ።

12) የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ማንኛውንም ወይም ሁሉንም ጨረታዎች ውድቅ የማድረግ፣ እንዲሁም ውል ከመሰጠቱ በፊት በማንኛውም ጊዜ የጨረታ ሂደቱን የመሰረዝ መብት ያለው ሲሆን፣ በዚህ ምክንያት ለተጫራቾች ምንም ዓይነት ኃላፊነት ወይም ተጠያቂነት አይኖርበትም።

አድራሻ፡ ኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ዋና መሥሪያ ቤት

ስልክ፡ 0115 180 175

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ።


Tender details

  • Deadline: 2026-07-08
  • Bid closing time: 14:00
  • Bid opening: 2026-07-08 14:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Ethiopian Red Cross Society
  • Buyer address: ሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሀይቅ ዳር ክ/ከተማ ጉዱ ማይሌ ቀበሌ ከዋና ማ/ቤት ጀርባ በኩል ነው።
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: Jun 24, 2026
  • Posted at: 2026-06-24T09:53:13.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders