የአማራ ሴቶች ማህበር በሥሩ ለሚገኝ ፕሮጀክት ተጠቃሚዎች ተገቢውን አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ተሽከርካሪ ይፈልጋል
Description
አማራ ሴቶች ማህበር
Amhara women Association
ቁጥር/Ref:- /አሴማ/08/ሰ/ለ-5
የተሽከርካሪ የጨረታ ማስታወቂያ
የአማራ ሴቶች ማህበር በሲቪል ማህበረሰብ አዋጅ ቁጥር 194/2004 አንቀጽ 63 (1) መሰረት የአማራ ሴቶች ማህበር የኢትዮጵያ ማህበር ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን የመዝገብ ቁጥር 016 ነው። የአማራ ሴቶች ማህበር በሁሉም የአማራ ክልል ዞን፣ ወረዳ እና ቀበሌ የተለያዩ የልማት ስራዎች የሚያከናውን ዘርፈ ብዙ የልማት ድርጀት ነው ሄርታታችን በአሁኑ ሰዓት ከ6 ፕሮጀክቶች በላይ በሁሉም ዞኖች፣ ወረዳ እና ቀበሌዎች በመተግበር ላይ ይገኛል። በዚህም መሠረት ድርጅቱ በሥሩ ለሚገኝ ፕሮጀክት ተጠቃሚዎች ተገቢውን አገልግሎት መስጠት የሚችሉ ተሽከርካሪ ይፈልጋል። በመሆኑም የተለያዩ ተሽከረካሪዎች ማቅረብ የሚችሉ ህጋዊ ተጫራቾችን ጨረታው ላይ እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
- ተጫራቾች በዘርፋ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማረጋገጫ /ክሊራንስ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች እነዚህን እና ሌሎች ተያያዥነት ያላቸውን ማስረጃወች ኮፒ በማድረግ በጀርባው ፊርማና ማህተም በማድረግ በማጫረቻ ሰነዳቸው ላይ ማካተት ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት ዓየር ላይ የሚቆይ ሲሆን ሰኔ 26/2018 ከሰአት 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት ጨረታዉ ባህር ዳር ባለው ዋና መ/ቤት ይከፈታል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ጨረታ ሰነዱን ሲወስዱ በሚሰጣቸው የዋጋ መሙያ ሰነድ ላይ ሞልተው ማለትም የዋጋ ሰነዳቸውን (በሰም በታሸገ ፖስታ ኤንቨሎፕ) ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተወዳዳሪዎች የፋይናንስ እና የቴክኒክ መስፈርቶችን በተለያዩ ፋይሎች በተዘጋጀ ሁኔታ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡበት ጊዜ /delivery time/ ውል ከተያዘበት ቀን ጀምሮ በ5 /አምስት/ ተከታይ ቀናት ውስጥ ብቻ ይሆናል።
- ተጫራቾች ሰነዱን ባህር ዳር በሚገኘው አማራ ሴቶች ማህበር ዋናው መ/ቤታችን ቀበሌ 13 ፖሊስ ኮሚሽን ፊትለፊት በጋዜጣዉ ላይ በተጠቀሱት ቀናት መሰረት ከጠዋት 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ከሰአት በኋላ 7፡00 ሰዓት ኣሰከ 10፡00 ሰአት የሚያገኙ ይሆናል። የጨረታ ሰነዱን ባህር ዳር በሚገኘው ዋና መ/ቤት ከፋይናንስ ክፍል መውሰድ ይችላሉ።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
ለበለጠ መረጃ፡ በስልክ ቁጥር 09 42 83 58 40/ 09 18 78 01 55
Tender details
- Deadline: 2026-06-29
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ጨረታው በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 የስራ ቀናት
- Bid opening: 2026-07-03 14:30
- Bid opening (note): ሰኔ 26/2018 ከሰአት 8፡30
- Region: Amhara
- Publishing entity: Amhara women Association
- Published: Jun 24, 2026
- Posted at: 2026-06-24T11:22:19.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.