የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ለአገልግሎት የሚውል የኤሌክትሮኒክስ፣ ህትመት፣ የመኪና ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ ለአገልግሎት የሚውል

  • የኤሌክትሮኒክስ፣
  • ህትመት፣
  • የመኪና ጎማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

 ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

  1. በዘርፉ በዘመኑ የታደለ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው።
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ሰርተፍኬት/ የሚያቀርቡ።
  3. የቫት ተመዝጋቢ የሆነ እና የቫት ሰርተፍኬት ኮፒ ማስያዝ አለበት።
  4. ከላይ በተ.ቁ 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ።
  5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ለሚወዳደሩት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲፒኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና የሚያስይዝ ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያው ከ500,000.00 ብር መብለጥ የለበትም።
  6. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት ቀናት እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 04 ድረስ በአካል ቀርቦ መግዛት ይቻላል።
  7. ማንኛውም ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳቡን በታሸገ ፖስታ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን እስከ 8:30 ድረስ አብክመ ጤና ቢሮ ግዥ ፋይ/ንብ/አስ ዳይሬክቶሬት ግዥ ክፍል ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግዥ ክፍል/ ጃይካ ህንፃ ጨረታው በወጣ በ16ኛው ቀን በ8:30 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 9፡00 ይከፈታል። ሆኖም ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በተከታዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል።
  9. ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡት ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
  10. ቢሮው የግዥውን መጠን እስከ 20% ሊጨምር ወይም ሊቀንስ ይችላል።
  11. የጨረታው አሸናፊ የሆነ ድርጅት ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሱ ወጪ ክልል ጤና ቢሮ መጋዘን ድረስ ማቅረብ አለበት።
  12. ቢሮው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  13. ስለ ጨረታው መረጃ ከፈለጉ አብክመ ጤና ቢሮ ግዥና ፋይ/ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ ቢሮ ቁጥር 06 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 058 222 1127 በመደወል ተጨማሪ መረጃ ማግኘት ይቻላል።

አብክመ ጤና ቢሮ /ባህር ዳር


Tender details

  • Deadline: 2026-07-13
  • Bid closing time: 14:30
  • Bid closing (note): ጨረታው በወጣ በ16ኛው ቀን በ8:30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-13 15:00
  • Bid opening (note): ጨረታው በወጣ በ16ኛው ቀን በ9:00 ሰዓት
  • Region: Amhara
  • Publishing entity: Amhara National Regional State Health Bureau
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 500.00 ብር
  • Published: Jun 27, 2026
  • Posted at: 2026-06-27T07:34:40.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders