የኢትዮጵያ የእንስሳት ሐኪሞች ማኅበር (Ethiopian Veterinary Association- EVA) በተመረጡ ክልሎች የሚገኙ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚውሉ የእንስሳት መድኃኒትና መገልገያ መሣሪያዎችን በአስቸኳይ ግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል
Description
የእንስሳት መድኃኒትና መገልገያ መሣሪያዎች ለመግዛት የወጣ
አስቸኳይ ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡ EVA/NCB/EV/02/2026
የኢትዮጵያ የእንስሳት ሐኪሞች ማኅበር (Ethiopian Veterinary Association- EVA) በተመረጡ ክልሎች የሚገኙ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ የሚውሉ የእንስሳት መድኃኒትና መገልገያ መሣሪያዎችን በአስቸኳይ ግልጽ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል።
በመሆኑም በዘርፉ የተሠማሩ፣ ብቃት ያላቸውና ከታች የተቀመጡ መሥፈርቶችን የሚያሟሉ አቅራቢዎችና አከፋፋዮች በጨረታው ላይ እንዲሳተፉ ማኅበሩ ይጋብዛል።
1. መቅረብ የሚገባቸው ሕጋዊ ማስረጃዎች
1.1. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድና የ2018 ዓ.ም ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣
1.2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) ምስክር ወረቀት፣
1.3. በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) መመዝገባቸው የሚያሳይ የምስክር ወረቀት፣
2. የጨረታ ሰነድ ግዥ ሂደት
2.1. ፍላጎት ያላቸው እና ብቁ የሆኑ ተጫራቾች ዝርዝር መረጃ የያዘውን የተሟላ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ባሉት 12 (አሥራ ሁለት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ በማኅበሩ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 303/306 ዘወትር በሥራ ሰዓት በአካል ቀርቦ ማግኘት ይችላሉ።
2.2. ሰነዱን መውሰድ የሚቻለው ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2:30 እስከ 6:30 እንዲሁም ከሰዓት በኋላ ከ7:30 እስከ 10:30 ባሉት የሥራ ሰዓታት ውስጥ ነው፦
2.3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% በጥሬ ገንዘብ፣ በባንክ በተረጋገጠ ቼክ ወይም CPO ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፣ ጨረታውን ያላሸነፉ ተወዳዳሪዎች ለጨረታው ዋስትና ያስያዙት ገንዘብ፣ ቼክ ወይም CPO አሸናፊ ድርጅት ከተለየ በኋላ ወዲያኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
2.4. ጨረታው በ12ኛው ቀን በ11፡30 ላይ ይዘጋል፣ በ13ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ላይ ተወዳዳሪዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የተጫራቾች ወይም የወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታውን መክፈት ሂደት አያስተጓጉልም።
2.5. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ፦
- በስልክ ቁጥር:- +251-115-525-020; 0911 894 90209; 0904 327 608; 0911 185 503
- አድራሻ፦ ከእንግሊዝ ኢምባሲ (British Embassy) ወደ School of Tomorrow በሚወስደው መንገድ 600 ሜትር ገባ ብሎ ይመናሹ ሕንጻ ፊት ለፊት።
የኢትዮጵያ የእንስሳት ሐኪሞች ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-07-09
- Bid closing time: 17:30
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በ12ኛው ቀን በ11፡30
- Bid opening: 2026-07-10 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በ13ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Ethiopian Veterinary Association
- Buyer address: ከእንግሊዝ ኢምባሲ (British Embassy) ፊት ለፊት 600 ሜትር ገባ ብሎ ወደ School of Tomorrow በሚወስደው መንገድ፣ ይመናሹ ሕንጻ አጠገብ እንገኛለን።
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Jun 28, 2026
- Posted at: 2026-06-30T06:37:04.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.