በአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአክሲዮን ጨረታ ማስታወቂያ አውጥቷል
Description
2ኛ የጨረታ ማስታወቂያ
በፍ/ባለመብት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና በፍ/ባለዕዳ እነወ/ሮ ሐወኒ አሸናፊ 2 ሰዎች መካከል ያለውን የአፈጻጸም ክስ ክርክር አስመልክቶ፡- አዋሽ 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ኃ.የተ.የግል ማህበር 3,808(ሶስት ሺህ ስምንት መቶ ስምንት) ለሆነ አክሲዮን እና የአንዱ አክሲዮን ዋጋ ብር 1000 (አንድ ሺህ) ከሆነ ውስጥ የፍርድ ባለእዳ የአክሲዮን ድርሻ በጥቅሉ 3,758(ሶስት ሺህ ሰባት መቶ ሃምሳ ስምንት) አክሲዮን የጠቅላላ አክሲዮን ዋጋ ብር 3,758,000(ሶስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሃምሳ ስምንት ሺህ) ሆኖ መግዛት የሚፈልግ አካል የመነሻውን ግምት ሃያ አምስት ብር 25% ሲፒኦ በማስያዝ ማህበሩ በሚገኝበት ቦታ ቀርበው ግልጽ በሆነ የጨረታ መነሻ ዋጋ በቀን 25/11/2018 ከጠዋቱ 3፡00 ሰአት እስከ 6፡30 ማህበሩ በሚገኝበት ቦታ የጨረታ ኮሚቴ መግዛት የሚፈልጉትን ሰዎች አወዳድሮ የሚሸጥ መሆኑን እየገለጽን፤ መግዛት የምትፈልጉ ቀርባችሁ መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
1. የጨረታው ማስታወቂያ አየር ላይ የሚቆየው ለተከታታይ ለ30 ቀናት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እና በኦሮሚያ ከለቻ ጋዜጣ፣ በአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግቢ ማስታወቂያ በሚለጠፍበት ቦታ እና በአዳማ ከተማ አስተዳደር ፊት ለፊት ተለጥፎ የሚቆይ ይሆናል።
2. መግዛት የሚፈልግ ሰው/ድርጅት/ ግምት ዋጋ ብር 3,758.000 (ሶስት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሀምሳ ስምንት ሺህ) የጨረታ መነሻ በሲፒኦ 25% አስይዞ መቅረብ አለበት።
በአዳማ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የፍትሐብሔር ጉዳይ ችሎት
Tender details
- Deadline: 2026-08-01
- Bid closing time: 12:30
- Bid opening: 2026-08-01 12:30
- Region: Oromia
- Publishing entity: Adama City Higher Court
- Bid bond: 25%
- Published: Jun 30, 2026
- Posted at: 2026-06-30T12:06:10.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.