የአምቦ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ኃ. የተ. ከአባላቱ ገዝቶ በአምቦ ከተማ መጋዘን ያከማቸውን ነጭ ጤፍ 2,774 + ኩንታል ሠርገኛ ጤፍ 1,350 + ኩንታል ቀይ ጤፍ 517 + በጠቅላላው 4,641 + ኩንታል በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
ለ3ኛ ጊዜ የወጣ
የእህል ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የአምቦ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ኃ. የተ. ከአባላቱ ገዝቶ በአምቦ ከተማ መጋዘን ያከማቸውን ነጭ ጤፍ 2,774 + ኩንታል ሠርገኛ ጤፍ 1,350 + ኩንታል ቀይ ጤፍ 517 + በጠቅላላው 4,641 + ኩንታል በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ተጫራቾቹ ማሟላት ያለባቸው ነገሮች
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ከዩኒያኑ ገበያ መምሪያ በብር 1000.00 መግዛት ይችላሉ።
- የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾቹ እህሎቹ ያሉበትን ሁኔታ አምቦ ከተማ በሚገኘው የዩኒያኑ መጋዘን በስራ ሰዓት በመገኘት ማየት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ በቅድሚያ 5% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው እንዳበቃ ለተሸናፊዎች ወዲያው የሚመለስላቸው ይሆናል።
- ጨረታው ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታተይ ቀናት አየር ላይ ከቆየ በኃላ በ8ኛው ቀን በ 4፡30 ሰዓት ጠዋት ታሽጎ በዛው ቀን ጠዋት በ 5፡00 ሰዓት ላይ አምቦ ባለው በዩኒየኑ ቢሮ ይከፈታል፡፡ 8ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥላው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል።
- ተጫራቾች ተወካዮቻቸው በጨረታው መክፈቻ ላይ ለመገኘት ከድርጅታቸው ህጋዊ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ተወዳዳሪዎች በሙሉ ባይገኙም በተገኘ ተጫራቾች ፊት ጨረታው በዕለቱ በሰዓቱ ይከፈታል።
- ተጫራቾች የመግዣ ዋጋቸውንና ለጨረታው የተጠያቁትን መረጃዎች በፖስታ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- አንድ ተጫራች በሌላው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይችልም፡፡ እንዲሁም ተጫራቹ ጨረታውን በአንዱ የእህል ዓይነት ወይም በሁሉም የእህል ዓይነት ላይ መጫረት ይችላል።
- ጨረታውን ያሸናፊ አሸናፊ ለውል ማስከበሪያ የጠቅላላውን ግዥ ዋጋ ባስያዘው የጨረታ “ማስከበሪያ /CPO/ ላይ 5% ለዋስትና በባንክ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
- ዩኒየኑ ለእህሉ ሽያጭ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ 0112609101 ወይም 0112363399 ይጠቀሙ
አምቦ የገበሬዎች ህብረት ሥራ ዩኒየን ኃ.የተወሰነ
Tender details
- Deadline: 2026-07-08
- Publishing entity: Ambo Farmer's Cooperative Union
- Bid bond: 5%
- Bid document price: 1000.00 ብር
- Published: Jul 01, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.