የባሶ ሊበን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የእንስሳት መድኃኒት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በምሥራቅ ጎጃም ዞን የባሶ ሊበን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት የገዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2018 በጀት ዓመት ለባሶ ሊበን ወረዳ እንስሳት ሃብት ጽ/ቤት አገልግሎት የሚወሉ
- የእንስሳት መድኃኒት
በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች
- ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና ፍቃዳቸውን ያሳደሱ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN ያላቸውና ማቅረብ የሚችሉ፤
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱ ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 25000/ሃያ አምስት ሺህ ብር በመሂ-1 በCPO ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ባሶ ሊበን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር-3 በመምጣት የማይመለስ 100 ብር ከፍለው መግዛት ይችላሉ።
- ይህ ግልፅ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ለ15 ቀን በአየር ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 3 በግልጽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የመክፈቻ ቀኑ በዓል ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል።
- በጨረታው አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለጸበት ቀን ጀምር ከ5 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ 10% በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡በተገለጸው የጊዜ ገደብ ያልቀረበና ውል ያልፈጸመ እንደሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙትን ገንዘብ መ/ቤቱ ውርስ ያደርጋል።
- ውድድሩ በሎት ወይም በጥቅል ዋጋ የሚለይ በመሆኑ ተጫራቾች ሁሉንም መሙላት እና በዋጋ መሙያ ሰነዱ ላይ የድርጅቱን ማህተም ስም እና ፊርማ ማድረግ ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊው ያሸነፈበትን ኦርጅናል መድኃኒቶችን ጽ/ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
- የባሶ ሊበን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በጨረታ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
- የመንግሥትን የግዥ መመሪያ አዋጅና ከላይ የተዘረዘሩትን ማዘዣዎች ያላሟላ ተጫራች ከውድድር ውጭ ይሆናል።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0582460316/0565 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአብክመ በምሥራቅ ጎጃም ዞን የባሶ ሊበን ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-07-16
- Publishing entity: Baso Liben Woreda FEDB
- Bid bond: 25,000.00 ብር
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: Jul 01, 2026
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.