የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈዉ የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

ግልጽና በሐራጅ ጨረታ ማስታወቂያ

የአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የጉምሩክ ህግን ተላልፈዉ የተያዙ የተለያዩ የኮንትሮባንድ እቃዎችን በቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት በቀን 01/11/2010 ዓ/ም እና 04/10/2018 በግልጽና በሐራጅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቶች የጨረታ ሰነዱን በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በአካል በመገኘት መግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሥም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት በተጫራች ስም የማይመለስ 100 (ቶ) ብር በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት ቦታ በቴሌግራም እንዲላክሎት በማድረግ ለጨረታ የቀረቡትን የእቃዎችን ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየት እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች በሟሟላትበጨረታው መሳተፍ የሚቻል ሲሆን የእቃዎችን ሳምፕል ከቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ከአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት፡እና በቴሌግራም ማየት የሚቻል መሆኑንና ወደ ቃሊቲ እንዲመጣልዎት የምትፈልጉት የእቃ ናሙና ካለ የጨረታ ማስታወቂያ በወጣበት ቀን በስልክ ቁጥር 022-224-1402 በመደወል ወደ ቃሊቲ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት እንዲመጣልዎት ማድረግ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።

የጨረታ መስፈርቶች፡

1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች በጨረታ በሚሸጡ ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርትፍኬት፣የዘመኑን ግብር የከፈለ ሰለ መሆኑ ክሊራንሰ (Clearance) እና የተጨማሪ እሴት ታክሰ እንቅሰቃሴያቸዉን ለታክሰ ማዕከሉ ያሳወቁበት፣በቅርብ ጊዜ የተሰጣቸዉ የምሰክር ወረቀት እና የመለያ ቁጥሩን ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ የሚችል።

2. ተጫራቾች የጨረታዉን ሰነድ ዘዉትር በስራ ሰዓት እስከ ቀን 01/10/2018 ዓ/ም እና 04/10/2018 ባሉት ቀናት ለግልፅ እስከ ጠዋቱ 3፡45 እንዲሁም ለሃራጅ ጨረታ በዚሁ ቀን እስከ ረፋዱ 5፡00 የእቃውን ዝርዝር የያዘ የጨረታ ሰነድ አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት በአካል በመገኘት በግዛት ወይም በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም በተከፈተ ቀጥታ አካውንት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በማስገባት የጨረታ ሰነድ ባሉበት በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይችላሉ።

3. ለግልፅ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (cpo) የሚወዳደሩበት እቃ ኮድ 5% እንዲሁም ለሃራጅ ጨረታ ለሚወዳደሩበት እቃ ኮድ ብር 100.000 (አንድ መቶ ሺ ብር) በባንክ አሰርተው በአዋሽ ጉምሩክ ቅ/ፅ/ቤት ስም ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

4. ተጨራቾች በሚከተለዉ የጨረታ ቀናት (እሰኬጁል) መሰረት በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት በመገኘት መጫረት ይችላሉ፡

የጨረታ ቦታ

የጨረታ ዓይነት

ለጨረታ የቀረቡ እቃዎች

የዕቃዎች መመልከቻ ቀን በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ

የጨረታዉ የመዝጊያ እና የመክፈቻ ቀንና ሰዓት

ቃሊቲ ጉምሩከ

ግልጽ እና ሃራጅ

ጫማዎች፣ አልባሳት፣ ኮስሞቲክስ፣ የመኪና መለዋጫ፣ ኤሌክትሪክ እቃዎች፣ ተሽከርካሪ መኪናዎች፣ የሞባይል ቀፎና አክሰሰሪ፣ ምግብነክ፣ እና ሌሎች ልዩ ልዩ እቃዎች

ለግልፅ ጨረታ እስከ 01/11/18 እሮብ እና 04/11/2018 ቅዳሜ ጠዋቱ 3:45 እና ለሃራጅ ጨረታ እስከ 445

ለግልፅ ጨረታ 01/10/18 እና 04/11/2018 ጠዋቱ 345 እና ለሃራጅ ጨረታ እስከ 500

5. የጨረታዉ መክፈቻ ቦታ በቃሊቲ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት የሚካሄድ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ወይም በታዛቢዎች ፊት ይከፈታል።

6. ለጨረታዉ አሸናፊ ተጫራቾች ለጨረታዉ ዋሰትና ያስያዙት (c.p.o) ከሚከፍሉት ዋጋ ጋር የሚታሰብላቸዉ ሲሆን ለተሸናፊ ተጫራቾች ደግሞ የጨረታ ዉጤት ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ በ3 የሰራ ቀናት ዉሰጥ ተመላሸ ይደረግላቸዋል።

7. ከአሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸዉ በደብዳቤ ከተገለጸላቸዉ ቀን ጀምሮ በ3 ቀናት ዉሰጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዉን በመረከብ ከመጋዝን ማውጣት ይኖርበታል።

8. ከላይ በተ.ቁ.7 በተገለጹት ቀናት ዉሰጥ ክፍያዉን ገቢ ያላደረጉ እና ንብረቱን ተረክበዉ ያልወሰዱ ተጫራቾች ለጨረታዉ ማሰከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ እና ለንብረቱ የከፈሉት ዋጋለኮሚሸኑ ገቢ ሆኖ ዕቃዉ በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

9. ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

  • ለተጨማሪ መረጃ በሰልክ ቁጥር 022-224-1402 ደዉለዉ ስለጨረታው መረጃ መጠየቅ ይቻላል።

አዋሽ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-11
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): የጨረታው ሰዓት ይለያያል
  • Bid opening: 2026-07-11 12:00
  • Bid opening (note): የጨረታው ሰዓት ይለያያል
  • Region: Oromia
  • Publishing entity: Awash Custom Commission Branch Office
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 100.00 /አንድ መቶ ብር/
  • Published: Jul 01, 2026
  • Posted at: 2026-07-01T08:06:03.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders