አይ ሲ ኤምሲ አጠቃላይ ሆስፒታል የሕክምና መገልገያ ዕቃዎችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ICMC/LO/H/004/2018/2026

አይ ሲ ኤምሲ አጠቃላይ ሆስፒታል ለሕፃናት ድንገተኛ ክፍል (PEDI ER)! ለሕፃናት ታካሚ ክፍል (PEDI WARD  ለሕጻናት ከፍተኛ እንክብካቤ ክፍል (PEDI ICU) እና ለሕጻናት የተመላላሽ ታካሚ ክፍል (PEDI OPD) የሚያገለግሉ የሕክምና መገልገያ ዕቃዎችን በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

ስለሆነም ክዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች በጨረታው እንድትሳተፉ ተጋብዛችኋል።

የተጫራቾች መወዳደሪያ መስፈርቶች እና መመሪያዎች፡

1. ሕጋዊ ሰነዶች፤ በዘርፉ የታደስ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2 የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (CPO)፡ ተጫራቾች በሚያስገቡት ጠቅላላ ዋጋ ከቫት (VAT) በፊት 2% (ሁለት በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በድርጅቱ ስም ከተረጋገጠ ባንክ የሚከፈል የክፍያ ትዕዛዝ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

የጨረታ ማስከበሪያው ጨረታው ፀንቶ የሚቆይበትን ጊዜ እና ተጨማሪ 28 (ሃያ ስምንት) ቀናትን የሚሸፍን ሆኖ መቅረብ አለበት።

3.የሰነድ አቀራረብ ተጫራቾች የቴክኒካል (Technical) እና የፋይናንሺያል (Financial) ሰነዶቻቸውን ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ ለይተው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

4. የጨረታ ሰነድ ግዢ፡ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ አምስተኛ ፎቅ በሚገኘው የፋይናንስ አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ፣ ለማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) ለአንዱ ሎት በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

5. የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ

  • ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) የሥራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ይዘጋል።
  • በዚሁ ዕለት ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 3ኛ ፎቅ በሚገኘው የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል
  • የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ፣ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ስዓት ተዘግቶ ይከፈታል።

6. የጨረታው ፀና የሚቆይበት ጊዜ፡ ጨረታው የሚፀናበት ጊዜ 60 (ስልሳ) የሥራ ቀናት ስለሆነ፣ ተጫራቾች ይህንን አውቀው መቀበላቸውን በኦሪጅናል የቴክኒካል ሰነዳቸው ላይ ማረጋገጥ (መግለጽ) አለባቸው።

7. የድርጅቱ መብት ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በዚህ ጨረታ አይገደድም፤ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ፀሀይ ሪል እስቴት ጀርባ

ለበለጠ መረጃ፦ በስልክ ቁጥራችን +251 91 287 3173 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።

አይ ሲ ኤምሲ አጠቃላይ ሆስፒታል


Tender details

  • Deadline: 2026-07-18
  • Bid closing time: 12:00
  • Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) የሥራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት
  • Bid opening: 2026-07-18 12:00
  • Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 (አስራ አምስት) የሥራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: International Cardiovascular Medical Center Share Company (ICMC )
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር) ለአንዱ ሎት
  • Published: Jul 01, 2026
  • Posted at: 2026-07-01T09:22:55.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders