የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ለፋብሪካው የተለያዩ ክፍሎች እና የእርሻ ማሽነሪዎች ተሸከርካሪዎች ጥገና የሚያስፈልጉ መለዋወጫዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር MSF/LP/09/2026
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተገለፁትን ለፋብሪካችን የተለያዩ ክፍሎች እና የእርሻ ማሽነሪዎች ተሸከርካሪዎች ጥገና የሚያስፈልጉ መለዋወጫዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
- ጥቅል አንድ፡- Bolt & Nut
- ጥቅል ሁለት ፡ Tip Top, Chain General use mat for garage(ለቲፕ ቶፕ እና ለሰንሰለት ብቻ ናሙና ይቅረብ)
- ጥቅል ሶስት - Electrical Materials
- ጥቅል አራት - Work Shop Tools
- ጥቅል አምስት - Graderversatile power plus Case tractor, Nissan Patrol Toyota ; Jhondeer; Ursus Tractor spare Parts
- ጥቅል ስድስት ፡ Toyota spare; Mitsubishi Spare, Yamaha spare, Suzuki Spare, Renault Spare & Chevrolet Spare Parts
- ጥቅል ሰባት ፤ Wooden Pole
በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል።
1. ሕጋዊ የንገድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፡ የዘመኑን የሀገር ውስጥ ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል።
2. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች ለእያንዳንዱ ጥቅል የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሠዓት ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ህንፃ ግዥ ቡድን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 215 የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ገዝተው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሲገዙ የንግድ ፈቃድ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል።
4. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሠነድ ጋር የታደሰ የንግድ ፈቃድ የአቅራቢዎች የምዝገባ ሠርተፍኬት እና ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእያንዳንዱ ጥቅል ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ) በሲ.ፒ.ኦ /C.P.O/ ወይም የባንክ ዋስትና /Bid bond guarantee/ በሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ አለባቸው፡ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ (Proforma invoice) ላይ በማዘጋጀት በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እ.ኢ.አ. ሐምሌ 09 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጧቱ 4፡00 ሠዓት ድረስ ሜክሲኮ ፊሊፕስ ሕንጻ ቢሮ ቁጥር 119 ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው በዕለቱ ሐምሌ 09 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢር ቁጥር 119 ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
6. ፋብሪካው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 011 550 5607, 011 550 5633
ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ሕንፃ
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ
አዲስ አበባ
Tender details
- Deadline: 2026-07-16
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-07-16 10:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Metehara Sugar Factory
- Bid bond: 50,000.00 ብር ለእያንዳንዱ ጥቅል
- Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ ጥቅል
- Published: Jul 02, 2026
- Posted at: 2026-07-02T07:40:21.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.