የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለሀረር ፊደራል ፖሊስ ሆስፒታል እና አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ Compound Light Pole & Lighting Fixture ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/EM/90/2026
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለሀረር ፊደራል ፖሊስ ሆስፒታል እና አፓርትመንት ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ Compound Light Pole & Lighting Fixture ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የዕቃውን ዓይነት |
የፕሮጀክት ስም |
የጨረታ ቁጥር |
የጨረታ መዝጊያ |
የጨረታ መክፈቻ |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
1 |
Compound Light Pole & Lighting Fixture |
ሀረር ፌዴራል ፖሊስ ሆስፒታል እና ግንባታ ፕሮጀክት |
DCE/ EM/90/2026
|
ሀምሌ 10/2018 ዓ.ም 4፡00 ሰዓት |
ሀምሌ 10/2018 ዓ.ም 4፡15 ሰዓት |
50,000.00
|
ስለሆነም፡-
- ተጫራቾች በዘርፍ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ፣የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ ፣ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ) እና የአገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ… ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከላይ በሠንጠዥ በተገለፀው መሠረት በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ለ120 (አንድ መቶ ሃያ) Calendar days ፀንቶ የሚቆይ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ቃሊቲ ቶታል ማደያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መኮድ ግቢ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ዋና መ/ቤት የግዥና ቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተያያዘው ዝርዝር እና ብዛት መሠረት መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡።
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
ቃሊቲ ቶታል ማደያ ዝቅ ብሎ የቀድሞ መኮድ ገቢ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 0114 403434
ማዞሪያ በ114-42:22-70/71/72
E-mail አድራሻ Info@dce-et.com
የድህረ ገፅ አድራሻ www.dce-et.com
ፖ.ሳ.ቁ 3414 ፋክስ ቁ.0114-400471/0114-
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
Tender details
- Deadline: 2026-07-17
- Bid closing time: 10:00
- Bid opening: 2026-07-17 10:15
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Defense Construction Enterprise (DCE)
- Buyer address: ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ
- Bid bond: 50,000.00 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jul 03, 2026
- Posted at: 2026-07-03T07:28:55.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.