አጋርፋ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ ኪንግ በርድ ስንዴ፣ አዶሻ ገብስ፣ ትራቭለር ገብስ፣ 1ኛ ደረጃ ዛላ በርበሬ እና 2ኛ ደረጃ ዛላ በርበሬ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የምርት ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የሸያጭ መለያ ቁጥር 04/01/2018 ዓ.ም.
አጋርፋ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ በ2017/2018 የምርት ዘመን ያመረተውን ኪንግ በርድ ስንዴ 3000(ሶሥት ሺህ ኩንታል)፤አዶሻ ገብስ 1000(አንድ ሺህ ኩንታል) ትራቭለር ገብስ 300(ሶስት መቶ ኩንታል) 1ኛ ደረጃ ዛላ በርበሬ 70(ሰባ ኩንታል)እና 2ኛ ደረጃ ዛላ በርበሬ 71.33(ሰባት አንድ ኩንታል ከ33/100) በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጹትን መመሪያዎች እና ግዴታዎችን በማሟላት መወዳደር ይችላሉ።
- ከመስኩ ጋር አግባብነት ያለው የታደሰ የእድሳት ጊዜው ያላለፈበት የሥራ ንግድ ፍቃድ፤
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ጊዜው ያላለፈበት የድጋፍ ደብዳቤ/የምስክር ወረቀት /ክሊራንስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ምርት የሰጠውን ጠቅላላ /ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ እና የዋስትና ጊዜው ከ2(ሁለት)ወር ያላነሰ የባንክ ዋስትና /CPO/BIDBOND/በኮሌጁ በአጋርፋ የግብርና ቴክኒክ የትምህርት ስልጠና ኮሌጅ ስም በማዘጋጀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ ከተገለጸለት በ5 (አምስት) ቀናት ወስጥ የውል ስምምነት ካልፈጸመ ፍቃደኛ እንዳልሆነ ተቆጥሮ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለኮሌጁ ገቢ ይሆናል።
- የተዘጋጀውን የመጫረቻ ሰነድ ከአጋርፋ ግ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ ከግዥና ፋይናንስ ስራ አስፈጻሚ ቢሮ እና አዲስ አበባ ሀይሌ ገ/ስላሴ ጎዳና በጌታነህ በሻህ ህንጻ በኩል ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ አዲስ ህይወት ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው አላጌ/ግ/ቴ/ሙ/ት/ሥልጠና ኮሌጅ ጉዳይ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ከሚገኘው የአጋርፋ ኮሌጅ ጉዳይ አስፈጻሚ ጽ/ቤት በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ 200 ( ሁለት መቶ) ብር በስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የስራ ቀናት ውስጥ መግዛት ይቻላል እንዲሁም የዋጋ ማቅረቢያቸውን ኦርጂናሉንና ኮፒውን በመለየት አስፈላጊ ከሆኑ ከተያያዥ የጨረታ ሰነዶች ጋር በፖስታ ውስጥ በማሸግ ከፍ ብሎ በተጠቀሰው አድራሻ አዲስ አበባ የኮሌጁ ጉዳይ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል።
- የጨረታው መዝጊያው ቀን እና የሚከፈትበት ቀን በተጨማሪ በጨረታ ሰነድ ላይ የሚገለጽ ሲሆን ተጫራቾች /ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ በኮሌጁ ጉዳይ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ውስጥ ይከፈታል።
- የጨረታው መክፈቻ ቀን እንደ አጋጣሚ ሆኖ በህዝባዊ ብሄራዊ በዓል ላይ የሚውል ከሆነ ጨረታው በቀጣይ የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰአትና ቦታ ይከፈታል።
- ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተነተርሶ ዋጋ መስጠት ተቀባይነት የለውም አይቻልም/።
- የምርቱን ናሙና ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ባሌ አጋርፋ የግብርና ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ አጋርፋ ቀርበው ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ በኮሌጁ እህል መጋዘን ማየት ይችላሉ።
- ኮሌጁ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ፡-ስልክ ቁጥር 0116625004 አዲስ አበባ ወይም 0911490870 0930108007 እና 0922319274 አጋርፋ የግ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ ደውለው መጠቀም ይችላሉ።
አጋርፋ የግብርና ቴክኒክናሙያ ትምህርትና ስልጠና ኮሌጅ
Tender details
- Deadline: 2026-07-14
- Bid closing time: 17:00
- Bid closing (note): ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 የስራ ቀናት ውስጥ
- Bid opening: 2026-07-14 17:00
- Bid opening (note): የጨረታው መዝጊያው ቀን እና የሚከፈትበት ቀን በጨረታ ሰነድ ላይ የሚገለጽ ይሆናል
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: አጋርፋ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jul 03, 2026
- Posted at: 2026-07-03T07:33:14.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.