በሰንፔር አክሲዮን ማኅበር የመማሪያ ክፍል ግንባታና የፓርቲሺን ስራ ማሰራት እንዲሁም ብዛት ያላቸው ፈርኒቸሮች (ዴስክ ወንበር፣ ጠረጴዛ ወዘተ) ግዢ እና የሚጠገኑ የፈርኒቸር እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ቁጥር 001/2019 የግንባታና ስራ እና የፈርኒቸር ግዢና ጥገና ግልፅ
የጨረታ ማስታወቂያ
በሰንፔር አክሲዮን ማኅበር በስሩ ለሚገኙት አቡነ ጴጥሮስ ትምህርት ቤቶች በሎት 1 እና በሎት 2 በተገለጹት ዘርፎች ላይ ግዢ ለመፈፀም እና ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።
- ሎት1 በት/ቤቶቹ ግቢ ውስጥ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍል ግንባታና የፓርቲሺን ስራ ማሰራት
- ሎት2. ለት/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ብዛት ያላቸው ፈርኒቸሮች (ዴስክ ወንበር፣ ጠረጴዛ ወዘተ) ግዢ እና የሚጠገኑ የፈርኒቸር እቃዎችን
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
1. በዘመኑ በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፊኬት ያላቸው።
3. የቫት ተመዝጋቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።
4. በመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ስር በአቅራቢነት የተመዘገቡበትን ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ።
5. ለግንባታና ፓርቲሽን ስራው የስራ ተቋራጭነት የስራ ልምድ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
6. ከላይ የተዘረዘሩትን ዶከመንቶች ኮፒ አድርጎ በማቅረብ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አብሮ ገቢ ማድረግ የሚችሉ።
7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በደረሰኝ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ውስጥ በአካል በመቅረብ መውሰድ ትችላላችሁ:: ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በአስራ አንደኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ተዘግቶ በአስራ አንደኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ይከፈታል።
8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሀሳቡን ያለ ስርዝ ድልዝ በግልጽ በመጻፍ አስከ አስረኛው ቀን 10፡00 ስዓት ዋና እና ኮፒ በፖስታ በማሽግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የተሞላው ዋጋ ለ60 ቀናት የሚቆይ ይሆናል።
9. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ (CPO)፣ ቢድ ቦንድ(BD Bond) ወይም በቼክ ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም አሸናፊ ድርጅቶች ውል በሚገቡ ሰዓት 10 ፐርሰነት የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
10. ተቋሙ ጨረታውን በሙሉም ይሁን በከፊል የመሰረዝ መብቱ እንደተጠበቀ ነው።
አድራሻ- አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ህንጻ ጎን KCBC ህንጻ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር B1-606/1 ለበለጠ መረጃ 0985 953 949/0987 972 785 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በሰንፔር አክሲዮን ማኅበር
Tender details
- Deadline: 2026-07-17
- Bid closing time: 12:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት በአስራ አንደኛው ቀን 3፡30 ሰዓት
- Bid opening: 2026-07-17 12:00
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት በአስራ አንደኛው ቀን 4፡00 ሰዓት
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: Sunper S.C
- Buyer address: አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ጎን KCBC ህንጻ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር B-606
- Bid bond: 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)
- Bid document price: 500.00 (አምስት መቶ ብር)
- Published: Jul 05, 2026
- Posted at: 2026-07-06T07:11:37.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.