የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት የዳቦ መጋገሪያ ማሽነሪ ከነጀነሬተሩ በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የመጀመሪያ ዙር የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ ሞዳሊቲ ለአቶ መሐመድ ቦራ ለሰጠው የዳቦ መጋገሪያ ማሽነሪ ከነጀነሬተሩ ተከራዩ የኪራይ ክፍያውን በካፒታል እቃ ዱቤ ግዥና ኪራይ ውል መሠረት ሊከፍል ባለመቻሉ በአዋጅ ቁጥር 103/1990 በተሠጠው ሥልጣን መሠረት በሐራጅ መሸጥ ይፈልጋል።
|
የሚሸጠው ንብረት |
የሐራጅ መነሻ ዋጋ በብር |
የሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
|||||
|
ተ.ቁ |
የንብረት አይነት |
ብዛት |
ንብረቱ የሚገኝበት ቦታ |
ቀን |
ሰዓት |
ቦታ |
|
|
1 |
Brade slicer |
(01) set |
በደ/ኢ/ክ/መ/ቡርጂ ዞን ሶያማ ከተማዐ2 ቀበሌ |
7,237,089.33 |
ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም |
4:00-6:00 |
በደ/ኢ/ክ/መ ቡርጂ ዞን ሶያማ ከተማ 02 ቀበሌ በአቶ ሞሃመድ ቦራ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይገኛል
|
|
2 |
Rotary oven |
14Tray |
|||||
|
3 |
Dough mixer |
(01) set |
|||||
|
4 |
Volumetric Dough Divider |
(01) set |
|||||
|
5 |
Molding Machine |
(01) set |
|||||
|
6 |
Flat tray with trolley |
(02) set |
|||||
|
7 |
French tray with trolley |
(02) set |
|||||
|
8 |
Diesel Generator 24kW |
(01) set |
|||||
ማሳሰቢያ፦
- ከላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች መግዛት የሚፈልግ ተደራዳሪ ተጫራች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ (25) በመቶ 1,809,272.33 (አንድ ሚሊዮን ስምንት መቶ ዘጠኝ ሺህ ሁለት መቶ ሰባ ሁለት ከ33/100) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ በማስያዝ በጨረታ ለመሳተፍ ይችላል።
- ማሸነሪው የተተከለ ሲሆን የሚሸጠው ማሽኑ ብቻ በመሆኑ አሸናፊው ካአሸነፈ በኋላ ማሽነሪውን ነቅሎ የመውሰድ ኃላፊነት ያለበት ሲሆን የማሽነሪውን መንቀያ እና የትራንስፖርት ወጭ የሚሸፈነው በአሸናፊው ነው።
- የሚሸጠው ንብረት የገባው ከቀረጥ ነጻ ስለሆነ ገዥው የቀረጥ ነጻ ተጠቃሚ እንዲሆን ባንኩ ድጋፍ ያደርጋል፡፡ ፈቃዱን ካላገኘ የቀረጥ ክፍያውን ገዥው ይከፍላል።
- ሐራጁ ሐምሌ 30 ቀን 2018ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ሰዓት ይከናወናል
- ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በካሽ ለሚገዙ ባሸነፉት ዋጋ ላይ የሚታሰብ የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ የታክስ ክፍያ ጨምሮ አሸናፊው ይከፍላል።
- አሸናፊው የሐራጁ አሸናፊ መሆኑ ከታወቀበት ጊዜ ጀምሮ ያለውን ማሸነሪዎችን ለማስጠበቅ የሚከፈል ክፍያ ለማሸነሪዎች መጠለያ ኪራይ እንዲሁም ተያያዥ ወጪዎች የመክፈል ግዴታ አለበት።
- አሸናፊው የባንኩን የሊዝ ፋይናንስን መስፈርት ካሟላ ሸያጩ በዱቤ ግዥ ይሆናል።
- አሸናፊው አሸናፊነቱ በደብዳቤ በተገለፀበት ቀን አንስቶ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል አለበት ካልከፈለ ባንኩ የሐራጅ ሸያጩን በመሰረዝ ለማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ በድጋሚ ይካሄዳል። በድጋሚ ሲሸጥ የሚፈጠረውን የዋጋ ልዩነት ይከፍላል።
- ሐራጁ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪል በተገኘበት ሐምሌ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ንብረቶቹ በሚገኝበት በቡርጂ ዞን ሶያማ ከተማ 02 ቀበሌ በአቶ ሞሃመድ ቦራ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይካሄዳል በሐራጁ ለመሳተፍ የሚፈልግ ተወዳዳሪ ሐራጁ በሚካሄድበት ቀን የሐራጅ ሰዓት ከመድረሱ በፊት ማለትም ከጠዋቱ 3፡00 ጀምሮ በሐራጅ ቦታ በመገኘት ምዝገባ ማካሄድ ሲ.ፒ.ኦ እና የታደሰ መታወቂያ ኮፒ ለጨረታ ኮሚቴ ማስረከብ አለበት።
- ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 046-181-06-06/03-03 ደውሎ ማግኘት ይቻላል። ንብረቶቹን በሥራ ሰዓት መጐብኘት የሚፈልጉ ተጫራቶች ካሉ ከዲስትሪክቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጐብኘት ይቻላል።
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ ለሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አርባምንጭ ዲስትሪክት
Tender details
- Deadline: 2026-08-06
- Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
- Bid bond: 25%
- Published: Jul 05, 2026
Categories
Other SalesSales, Disposals and ForeclosureKitchen EquipmentEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsIndustrial Machinery Provision and InstallationGeneratorsEnergy, Power and ElectricityMachinery and EquipmentAgriculture and FarmingVehicle and Machinery SaleVehicle and Machinery ForeclosureAmharic2merkatoDevelopment Bank of EthiopiaSouth Ethiopia Regional State
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.