በኬሚካል ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሣ ኬሚካል ፋብሪካ የምርት ማሸጊያ ማዳበሪያ በጥራትና በብቃት አምርቶ ለማቅረብ ልምድ፣ ችሎታና ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል

Description

ድጋሚ የወጣ ጨረታ ማስታወቂያ 

ቁጥር ኬኢኮአመኬፋ 012/2018

በኬሚካል ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሣ ኬሚካል ፋብሪካ ከታች የቀረቡትን የምርት ማሸጊያ ማዳበሪያ በጥራትና በብቃት አምርቶ ለማቅረብ ልምድ፡ ችሎታና ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾችን አወዳድሮ ማስራት ይፈልጋል።

ብዛቱ 83,200 ባለ 50 ኪሎ ግራም የአሉሚኒየም ሳልፌት ምርት ማሸጊያ ማዳበሪያ ከረጢት ድርጅቱ በጨረታ ሰነዱ ባስቀመጠው ዝርዝር መግለጫ መሰረት ከሀገር ውስጥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። 

ስለሆነም ፡

1. ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን የ/2018 ዓ.ም/ ግብር የከፈሉ፣ በአቅራቢዎችዝርዝር የተመዘገቡ፡ የታክስ ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ሰነዳቸውን በማቅረብ ጨረታውን መሣተፍ ይችላሉ፣

2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከአዲስ አበባ ሳሪስ አቦ መርቲ ህንጻ የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ሽያጭ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤትእና ከአዋሽ መልካላ ኬሚካል ፋብሪካ ከግዥ ከፍል ዘወትር በስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ መግዛት ይችላሉ፣

3. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ወይም በባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ማቅረብ አለባቸው፣

4. ተጫራቾች ሁለት የማዳበሪያ ከረጢት ናሙና የማይመለስ ከቴክኒካል አፈርና ከላይ በተራ ቁጥር 1 እና 3 የተገለጹትን ማስረጃዎች በአንድ ፖስታ፣ ከዚህ በተጨማሪ ፋይናንሻል ኦፈር ለብቻ በአንድ ፖስታ ታሽገው አዲስ አበባ ሳሪስ አቦ መርቲ ህንጻ የአዋሽ መልካሳ ኪሚካል ፋብሪካ ሽያጭ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት እስከ ሀምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ሰነዶቹን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ እለት በ4፡00 ይዘጋል።

5. ጨረታው ሀምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ከቴክኒካል ኦፈሩ ብቻ በ4፡30 በአዲስ አበባ ሳሪስ አቦ መርቲ ህንጻ የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ሽያጭ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን መክፈት አያግድም። ቴክኒካል ምዘና ናሙና ፍተሻ በድርጅቱ በራሱ ይከናወናል።

6. ማዳበሪያ ከረጢቱ ተፈትሾ ቴክኒካል ምዘና ያለፉት ተጫራቾች ብቻ ፋይናንሻል ኦፈራቸው ሀምሌ 24 ቀን 2018 ዓ.ም በ4፡00 ሰአት በአዲስ አበባ ሳሪስ አቦ መርቲ ህንጻ የአዋሽ መልካሳ ኪሚካል ፋብሪካ ሽያጭ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን መከፈት አያግድም።

7. አዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- ስልክ 011 554 5771 / 0920 935 336

በኬሚካል ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሣ ኬሚካል ፋብሪካ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-24
  • Bid closing time: 10:00
  • Bid opening: 2026-07-24 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: በኬሚካል ኢንዳስትሪ ኮርፖሬሽን- የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ (ኬኢኮ-አመኬፋ)
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Jul 05, 2026
  • Posted at: 2026-07-06T10:48:36.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders