በኬሚካል ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሣ ኬሚካል ፋብሪካ መኪናዎች በጥራትና በብቃት ለማቅረብ ልምድ፣ ችሎታና ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Description
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር ኬኢኮአመኬፋ 010/2018
በኬሚካል ኢንደስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሣ ኬሚካል ፋብሪካ ከታች የቀረቡትን መኪናዎች በጥራትና በብቃት ለማቅረብ ልምድ፡ ችሎታና ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
ብዛት ሁለት መኪናዎች ሎት 1፡- አንድ ደብል ፒካፕ መኪና ሎት 2 አንድ ሎደር ድርጅቱ በጨረታ ሰነዱ ባስቀመጠው ዝርዝር መግለጫ መሰረት ከሀገር ውስጥ በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆንም።
1. ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን የ/2018 ዓ.ም/ ግብር / የከፈሉ፣ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፡ታከስ ክሊራንስ እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ፣
2. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ከአዲስ አበባ ሳሪስ አቦ መርቲ ህንጻ የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ሽያጭ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤትና ከአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ከግዥ ክፍል ዋናው መስሪያ ቤት ዘወትር በስራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ መግዛት ይችላሉ፣
3. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% ያላነሰ የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ወይም በባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.አ ማቅረብ አለባቸው፣
4. ተጫራቾች ከቴክኒካል አፈርና ከላይ በተራ ቁጥር 1 እና 3 የተገለጹትን ማስረጃዎች በአንድ ፖስታ፣ ከዚህ በተጨማሪ ፋይናንሻል ኦፈር ለብቻ በአንድ ፖስታ ታሽገው በአዲስ አበባ ሳሪስ አቦ መርቲ ህንጻ የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ሽያጭ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት እስከ ሀምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ ሰነዶቹን ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ እለት በ5፡00 ይዘጋል።
5. ጨረታው ሀምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም የቴክኒካል ኦፈሩ ብቻ በ5፡30 በአዲስ አበባ ሳሪስ አቦ መርቲ ህንጻ የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ሽያጭ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ቢሮ ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን መከፈት አያግድም።
6. ቴክኒካል ምዘና ያለፉት ተጫራቾች ብቻ ፋይናንሻል ኦፈራቸው ሀምሌ 24 ቀን 2018 ዓ.ም በ5፡00 ሰአት በአዲስ አበባ ሳሪስ አቦ መርቲ ህንጻ የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ሽያጭ ቅርንጫፍ መስሪያ ቤት ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን መክፈትአያግድም።
7. አዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡- ስልክ 011 554 5771 / 0920 935 336
በኬሚካል አንደስትሪ ኮርፖሬሽን የአዋሽ መልካሣ ኬሚካል ፋብሪካ
Tender details
- Deadline: 2026-07-24
- Bid closing time: 11:00
- Bid opening: 2026-07-24 11:30
- Region: Addis Ababa
- Publishing entity: በኬሚካል ኢንዳስትሪ ኮርፖሬሽን- የአዋሽ መልካሳ ኬሚካል ፋብሪካ (ኬኢኮ-አመኬፋ)
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Jul 05, 2026
- Posted at: 2026-07-06T10:51:05.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.