ሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን Tyre with inner tube ለመግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ
ሀገር አቀፍ ግልፅ ጨረታ ቁጥር 03/2018

ሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን ተጫራቾች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

.

የዕቃው ዓይነት

ምርመራ

ሎት 1

Tyre with inner tube 12.00*20

 

ሎት 2

Tyre with inner tube 12.00*22.5

 

በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች

  • በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ፍቃድ ያላቸው
  • ቫት የተመዘገቡ
  • በጨረታ ለመሣተፍ ከገቢዎች ፍቃድ ያላቸው
  • የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
  • የጨረታ ሰነድ የሚሸጥበት ጊዜና ቦታ

1. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15 ተከታታይ ቀናት ድረስ የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የሂሳብ ቁጥር 1000604259658 በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ገቢ በማድረግ የንግድ ፍቃዳቸውን ፎቶ ኮፒ ይዘው በመቅረብ ከግዥና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይቻላሉ። ጨረታው የሚከፈትበት እና ሰነዱ የሚቀርብበት ጊዜ

1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸውን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከቀኑ ከ8፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ያስገባሉ።

2. በማግስቱ በ17ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

3. ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።

የጨረታ ዋስትና ፦

1. ማንኛውም ተጫራች 2% በባንክ የተረጋገጠ CPO ወይም ከስድስት ወር ያላነሰ ጊዜ ያለው በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ቢድቦንድ ዋስትና ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል።

የጨረታ ሠነድ አስተሻሸግ ሁኔታ

1. የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማስረጃ ፣ የልዩ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነትና የታክስ ክፍያ ማረጋገጫ ሰነዶች፣ በጨረታው ለመሳተፍ ከገቢዎች የተሰጠ ማስረጃ እና የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተደገፈ CPO/ ከኦርጂናል የዋጋ ማቅረቢያ ጋር በአንድ ላይ በሰም ታሽገው መቅረብ አለባቸው። ፋይናንሻል ሰነዶች ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በስም ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል።

2. ቴክኒካል ሰነዶች ኦርጅናልና ኮፒ ለየብቻ በሰም ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል። ይህንን አስተሻሸግ ዘዴ ያልተጠቀመ ተጫራች ከጨረታው ይሠረዛል። ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 16 07 15 39/ 09 11 80 67 09 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ። ኮርፖሬሽኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የሲዳማ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን


Tender details

  • Deadline: 2026-07-21
  • Publishing entity: Sidama Construction Works Corporation
  • Bid bond: 2%
  • Bid document price: 300.00 (ሶስት መቶ ብር)
  • Published: Jul 06, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders