አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ የፕላስቲክ ምርቶች መካከል Geomembrane Sheet የተባለውን ምርት በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Description
የምርት ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር-APF/28/2018 /Local
አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ ከሚያመርታቸው የፕላስቲክ ምርቶች መካከል Geomembrane Sheet የተባለውን ምርት በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ከሐምሌ 01/2018 እስከ መስከረም 30/2019 ዓ.ም ድረስ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ ምርቱ ውሃ ለማቆር እና ለሌሎች የግብርና ስራዎች አገልግሎት የሚውል፤ መልኩ ጥቁር(Dark Black) ውፍረቱ 0.4ሚ.ሜ ሲሆን ለሽያጭ የቀረበው ጠቅላላ ብዛት 1,200,000 ካሬሜትር ሆኖ በሎት እንደሚከተለው ከዚህ በታች ተቀምጧል።
- ሎት1 ያልተበየደ ብዛት 1,020,000 ካ.ሜ፡-
የዚህ ምርት ርዝመት 28 ሜትር ወርድ 6.25 ሜትር ሲሆን ስፋቱ 175 ካሬ ሜትር ነው።
የዚህ ምርት የአንድ ካሬ ሜትር መነሻ የጨረታ ዋጋ ከነቫቱ ብር 228.57 ነው።
- ሎት 2 የተበየደ ብዛት 180,000 ካ.ሜ፡-
የዚህ ምርት ርዝመት 14 ሜትር ወርድ 12.5 ሜትር ሲሆን ስፋቱ 175.36 ካሬ ሜትር ነው፡፡ የዚህ ምርት የአንድ ካሬ ሜትር መነሻ የጨረታ ዋጋ ከነቫቱ ብር 230.00 ነው።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን የጨረታ መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
- ተጫራቾች ለ2018 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና ተያያዥ የሆኑ የሕጋዊነት ሠነዶችን ማለትም የንግድ ምዝገባ ሰርተፊኬት፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት (TIN) እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት ቅጅ (Copy) ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ለተወዳደሩበት ለእያንዳንዱ ሎት ማለትም፡- ለሎት 1 ብር 1,000,000.00፣ ለሎት 2 ብር 150,000.00 የጨረታ ማስከበሪያ በፋብሪካው ስም በማሰራት ማቅረብ አለባቸዉ።
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል ከፋብሪካው የፋይናንስ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 105 ማግኘት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን የሕጋዊነት ሠነዶቻቸውን ቅጅ (Copy) የመወዳደሪያ ዋጋቸውን ፣ የጨረታ ማስከበሪያ እና ሌሎችን ማስረጃዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ቢሮ ቁጥር 206 ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠር በ10ኛው ቀን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቢሮ ቁጥር 206 ከቀኑ 8፡00 ላይ ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡ በጨረታው መክፈቻ ዕለት የሚገኙት የተጫራች ድርጅቶች ተወካይ ወይም ባለቤት ህጋዊ የፍትሕ ውክልና ወይም የድርጅቱ ባለቤት ወይም ሠራተኛ ስለመሆኑ ከድርጀቱ የተፃፈ ደብዳቤ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው።
- 10ኛው ቀን ሕዝባዊ በዓል ወይም የእረፍት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ተዘግቶ የሚከፈት ይሆናል።
- የውድድሩ አሸናፊ የሚለየው በየሎቱ ሲሆን በሎቱ ለተጠቀሰው ምርት ለአንድ ካሬ ሜትር ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች የውድድሩ አሸናፊ ይሆናል።
- አሸናፊዎች ምርቱን ለማንሳት በቅድሚያ ለሎት ብር 2,000,000.00 ለሎት 2 ብር 300,000.00 ዋጋ ያለው የውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በፋብሪካው ስም በማሰራት ወይም በጥሬ ገንዘብ በማቅረብ አሸናፊነታቸው ከተገለጸበት እለት ጀምሮ ባሉት በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የውል ስምምነት የመፈፀም ግዴታ አለባቸው።
- በየወሩ ማለትም በሐምሌ፣ በነሐሴ እና በመስከረም ወራት የሚነሳው የምርት መጠን እንደቅድምተከተሉ 500,000 ካ.ሜ፣ 400,000 ካ.ሜ፣ 300,000 ካ.ሜ ነው፡፡ ስለሆነም የውድድሩ አሸናፊዎች ምርቱን ለማንሳት በቅድሚያ በየወሩ የሚያነሱትን ምርት ጠቅላላ ዋጋ የተጨማሪ እሴት ታክስ ጨምሮ 50% ውል በተያዘ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ገቢ የማድረግ ግዴታ አለባቸው።
- ፋብሪካው ማንኛውንም ዓይነት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ 09-35-98-37-29/ 09 00 90 92 50 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አማራ ፓይፕ ፋብሪካ ኃላ/የተ/የግል ኩባንያ
ባህርዳር
Tender details
- Deadline: 2026-07-16
- Publishing entity: Amhara Pipe Factory PLC
- Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
- Bid document price: 500.00 ብር
- Published: Jul 07, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.