የወርቅ አምባ ንግድ እና አፓርታማ አ.ማ. በባሕር ዳር ከተማ እየገነባ የሚገኘው B+G+14+T ንግድና አፓርትመንት ህንጻ ግንባታ የቁፋሮ ስራው የተጠናቀቀ ሲሆን አክሲዮኑ ሊሰራዉ ያሰበዉን የፉቲንግ ፓድ የኮንክሪት ሙሊት ስራ በሙያዉ ልምድ ያላቸውን ደረጃ GC/BC-5 እና በላይ የሆኑ ሥራ ተቋራጮችን በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል
Description
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የወርቅ አምባ ንግድ እና አፓርታማ አ.ማ በባሕር ዳር ከተማ እየገነባ የሚገኘው B+G+14+T ንግድና አፓርትመንት ህንጻ ግንባታ የቁፋሮ ስራው የተጠናቀቀ ሲሆን አክሲዮኑ ሊሰራዉ ያሰበዉን የፉቲንግ ፓድ የኮንክሪት ሙሊት ስራ በሙያዉ ልምድ ያላቸውን ደረጃ GC/BC-5 እና በላይ የሆኑ ሥራ ተቋራጮችን በማወዳደር ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በስራው ሂደት አክሲዮን ማህበሩ ለስራው የሚያስፈልጉ ዋና ዋና ማቴሪያሎችን ማለትም ብረት፣ ሲሚንቶ፣ አሸዋ፣ ጠጠር፣ ውሃ እና የአናጺ ሽቦ የሚያቀርብ መሆኑን እያሳወቅን ከተዘረዘሩት ማቴሪያሎች ውጭ ሎሎች ለግንባታው አስፈላጊ የሆኑ ማለትም የሰው ሃይል፣ ፎርም ወርክ፣ ሮለር፣ ሚክሰር፣ ቫይብሬተር፣ እንጨት፣ ሚስማር፣ ውሃ ማጠጣትና ለራሱ ማቴሪያል ማስቀመጫ የሚሆን ስቶር መገንባት እና ሌሎች ማቴሪያሎችን ጨምሮ በስራ ተቋራጩ የሚቀርብ መሆኑን ታዎቆ ይህንንም ከጨረታ ሰነዱ ጋር በደብዳቤ አረጋግጦ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
በዚህም መሰረት፡-
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (የቲን) ሰርተፊኬት እና የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ሰርተፊኬት ተመዝጋቢ ስለመሆኑ እና የዘመኑን ግብር ስለመከፈሉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የስራ ልምድ ቢያንስ 5 አመትና በላይ ያላቸው ሳይት መሃንዲስ መመደብ የሚችሉ እና ሊሰራ ከታሰበዉ ስራ ጋር ተመሳሳይ ቢያንስ ሁለት ፕሮጀክቶች የሰራና ለሰራዉ ስራ የተሰጠ የመልካም ስራ አፈጻጸም ማስረጃ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አባሪ አድርጎ በደብዳቤ አረጋግጦ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሃሳቦቻቸዉን ፋይናንሻል እና ቴክኒካል የሰሯቸውን ስራዎች የሚገልጽ ማስረጃ ዋናውንና ኮፒዉን በተለያዩ ፖስታዎች በጥንቃቄ በማሸግ ከላይ በሌላ አንድ ፖስታ በማድረግ ይህ ጨረታ ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ ፖስታው ላይ ፊርማ እና ማህተም በማድረግ ከአክሲዮኑ ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ግዥ ጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በአሰሪው የወርቅ አምባ ንግድ እና አፓርታማ አ.ማ ስም በታሸገ ፖስታ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ ቀናት ድረስ ክፍት ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጥዋቱ በ4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ መኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ እለቱ የበዓል ቀን/ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡
- አሸናፊዉ ድርጅት ከተለየ በኋላ ለግንባታ ስራዉ አፈጻጸም ዋስትና ፐርፎርማንስ ቦንድ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ አሸናፊነቱ በተገለጸበት በ5 /አምስት/ ቀናት ውስጥ የባንክ ዋስትና ውል በማስያዝ ውል መውሰድ ይኖርበታል፡፡
- አሸናፊዉ ተጫራች ቅድመ ክፍያ እንዲሰጠዉ የሚፈልግ ከሆነ ከአሸነፈበት ዋጋ 15 በመቶ የሚደርስ ቅድመ ክፍያ ሊጠይቅ ይችላል፡፡ ሆኖም ቅድመ ክፍያዉ የሚሰጠው ከጠየቀው ቅድመ ክፍያ መጠን ጋር ተመጣጣኝ የሆነ ዋስትና ከታወቀ ባንክ በተረጋገጠ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና /unconditional bank guarantee/ ማቅረብ ሲችል ብቻ ነው፡፡
- አክሲዮኑ ሊያሰራ የፈለገዉን መጠን በስራ ዝርዝሩ ላይ የተቀመጠ ቢሆንም የመጠን ለዉጥ ሊኖር የሚችል ማለትም ሊቀንስም ሊጨምርም እንደሚችል መታወቅ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ተመላሽ የማይደረግ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል ከወርቅ አምባ ንግድ እና አፓርታማ አ.ማ ቢሮ ቁጥር 314 ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የወርቅ አምባ ንግድ እና አፓርታማ አ.ማ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +2519 10 20 19 94 / +2519 79 15 62 00 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የወርቅ አምባ ንግድ እና አፓርታማ አ.ማ
Tender details
- Deadline: 2026-07-15
- Publishing entity: ወርቅ አምባ ንግድ እና አፓርታማ አ.ማ
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: Jul 06, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.