በአብክመ በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳድር የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ እንስሳት አሳ ሀብት ልማት ጽ/ቤት ለእንስሳት ጤና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የእንስሳት መድኃኒቶችን ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳድር የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ እንስሳት አሳ ሀብት ልማት ጽ/ቤት ለእንስሳት ጤና አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የእንስሳት መድኃኒቶችን ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ካላቸው ድርጅቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ አቅራቢዎች እንድትሳተፉ ይጋብዛል።
- የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው /ያላት/
- በዘርፉ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው /ያላት/
- የታደሰ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ያለው /ያላት/
- የመደኃኒቶች መገልገያ ማብቂያ ጊዜ /Exp. Date/ ሁለት /2/ አመት የቀረው መሆን አለበት።
- ተጫራቾች በአንዱ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ በባንክ በተመሰከረለት ትክክለኛ ሲፒኦ ወይም በህጋዊ ደረሰኝ /መሂ-1/፡- ማስያዝ አለባቸው።
|
ሎት |
የጨረታው ዓይነት |
የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ |
የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና |
|
1 |
የእንስሳት የህክምና መደኃኒት |
100 |
40,000 |
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከሚዘጋበት ድረስ ባሉት ተከታታይ ቀናት ውስጥ ከላይ የተጠቀሰውን የጨረታ ሰነድ መሸጫ ዋጋ የማይመለስ ብር 100/አንድ መቶ/ በመክፈል ከ ሲ/ዋዩ ወ/እን/አሳ/ሀብት/ጽ/ቤት እንስሳት ጤና ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለተጫራቾ ክፍት ሆኖ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ታሽጎ በዕለቱ ከጠዋቱ 4፡10 ተጫራቾች ቢገኙም ባይገኙም የሚከፈት ሲሆን ዕለቱ የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀናት በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
- ማንኛውም ተጫራች የሚጫረትበትን ዋጋ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ካለምንም ስርዝ ድልዝ በመሙላት ኦርጅናሉን ብቻ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በፖስታው ላይ ስማቸውን፣ አድራሻቸውን እና የሚወዳደሩበትን የጨረታ ዓይነት በመፃፍ ሲዋዩ /ወ እን አሳ/ሀብት/ጽ/ቤት እንስሳት ጤና ቡድን ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከ ሚዘጋበት ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈባቸው የእንስሳት መድኃኒቶች በራሱ ወጪ በማጓጓዝ በጽ/ቤቱ በሚገኙ ንብረት ክፍል ገቢ ያደርጋል።
- አሸናፊው ተጫራች አሸናፊነቱ በማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ካሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% በባንክ በተመሰከረ ትክክለኛ ሲፒኦ ወይም በህጋዊ ደረሰኝ /መሂ-1/ በማስያዝ ውል ይፈጽማል።
- መ/ቤቱ በግዥው ላይ 20% የመጨመር እና የመቀነስ መብት አለው።
- መ/ቤቱ ጨረታውን በጥቅል ዋጋ ላይ የተመሰረተ አድርጎ ያወዳድራል።
- መ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 620 0661 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በአብክመ በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳድር የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ እንስሳት አሳ ሀብት ልማት ጽ/ቤት
Tender details
- Deadline: 2026-07-22
- Bid closing time: 10:00
- Bid closing (note): ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት
- Bid opening: 2026-07-22 10:10
- Bid opening (note): ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡10 ሰአት
- Region: Amhara
- Publishing entity: በአብክመ በሰሜን ሸዋ ዞን መስተዳድር የሲያደብርና ዋዩ ወረዳ እንስሳት ሀብት ልማት ማ/ተ/ጽ/ቤት
- Bid bond: 40,000.00 ብር
- Bid document price: 100.00 ብር
- Published: Jul 07, 2026
- Posted at: 2026-07-07T08:28:12.000Z
Documents
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.