መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን ኃ.የተ. የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል
Description
ለመጀመሪያ እና ለሶሰተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ
የጨረታ ማስታወቂያ
በአብክመ በባሕር ዳር ከተማ ቀበሌ 15 የሚገኘው መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን ኃ.የተ.
- ሎት 1. የሰብል ሙቀት መለኪያ (Mositure Meter)፣ ለሶሰተኛ ጊዜ
- ሎት 2. ሚዛን ባለ መቶ የሚመዘን ለሶሰተኛ ጊዜ፣
- ሎት 3. የሩዝ መዝሪያ ማሽን ለሶሰተኛ ጊዜ
- ሎት 4. ሲልፎስ ግዥ ለመጀመሪያ ጊዜ፣
- ሎት 5. የቤት ማስዋቢያ የተለያዩ ዕቃዎች ግዥ ለመጀመሪያ ጊዜ፣
- ሎት 6. የመኪና መለዋዋጫ ዕቃዎች ግዥ ለመጀመሪያ ጊዜ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሽናፊው መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን) ያላቸው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ ሁለት በመቶ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረት የባንክ ጋራንቲ ወይም (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ የተያዘ ከሆነ ደረሰኙ ከዋጋ ማቅረቢያው ፖስታው ውስጥ በማስገባት ማያያዝ አለባቸው፡፡
- ጨረታው ከብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና በላይ ዋጋ የሚሆን ከሆነ በተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት እንዳይሰበሰብባቸው ፈቃድ የተሰጣቸው (በግብር አዋጁ ከግብር ነጻ ከሆኑ) አቅርቦቶች ካልሆኑ በስተቀር በግዥው የሚሳተፉ ማንኛውም ተጫራቾች በተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማያያዝ አለባቸው፡፡ እንዲሁም ዋጋ ሲሞላ እና ሲፒኦ ሲያሲይዙ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡ ቫት የሚጠይቀው የአንዱ ወይም በጥቅል (ሎት) የሚገዛው እቃ እንጂ በአንድ ማስታወቂያ ለወጡ አይደለም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች አንዱ ባቀረበው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ላይ ክብ ማህተም በማድረግ እና ለጨረታው የሚያስፈልጉ ሰነዶች በፖስታው ውስጥ ማስገባትና ፖስታው ላይ ክብ ማህተም በማድረግ በጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
- በጨረታው ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 350 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ማስታቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ለወጣው ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ለሶሰተኛ ጊዜ ለወጣው ለ7 ተከታታይ ቀናት ከዩኒየኑ ሒሳብ ክፍል ወይም ቢሮ ቁጥር 106 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለመጀመሪያ ጊዜ ለወጣው ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 10ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ10ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡ ለሶሰተኛ ጊዜ ለወጣው ለ7 ተከታታይ ቀናት ፀንቶ የሚቆይ ሲሆን እስከ 7ኛው ቀን እስከ 8፡00 ድረስ የመወዳደሪያ ሰነዶችን ዩኒየኑ ባዘጋጀው ፖስታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው በ7ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በዚሁ እለት 8፡30 ላይ የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ቅዳሜ ዩኒየኑ የሥራ ሰዓት ሲሆን ጨረታው በሚከፈትበት ቀን በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በዚሁ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡
- የጨረታው ተወዳዳሪዎች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተወዳዳሪዎች ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ አለመገኘት
ጨረታውን ከመክፈት አያግደውም፡፡ - የጨረታው አሽናፊው በጨረታ ማሸነፉ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በ5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አሽናፊው የውል ማስከበሪያ ተቀባይነት ባላቸው የዋስትና ዓይነቶች የጠቅላላ የውሉን ዋጋ 10 በመቶ በማስያዝ ውል መፈጸም አለበት፡፡
- የሚፈልጉትን ሎት መርጦ መሙላት የሚቻል ሲሆን ከአንድ ሎት ውስጥ ለይቶ ወይም ቀንሶ ወይም መርጦ መሙላት አይቻልም፡፡ አሸናፊው የሚለየው በተናጥል ይሆናል፡፡ የሎት 5 አሸናፊ የሚለየው በጥቅል ዋጋ ይሆናል፡፡ አሽናፊው የአሸነፈውን እቃ በፍትህ ውል ከተመረመረ ወይም ከተመዘገብ የምርመራም ሆነ የምዝገባ ክፍያ አሸናፊው ይከፍላል፡፡
- አሸናፊው የአሸነፈውን እቃ በእራሱ ትራንስፖረት አጓጉዞ ያቀርባል፡፡ ለሰራተኛም ሆነ ለትራንስፖርት ማንኛውንም ወጭ አሸናፊው
ይሸፍናል፡፡ የሚገዙት የማንኛውም እቃዎች መጠንና (ስፔስፊኬሽን) ከጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፡፡ - ያልተጠቀሱ ሀሳቦች ቢኖሩ በአብክመ ህ/ስ/ማ የግዥና ሽያጭ መመሪያ ቁጥር 58/2015 መሰረት የሚስተናገዱ ይሆናሉ፡፡
- ዩኒየኑ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ለበለጠ መረጃ በአካል ወይም በስልክ ቁጥር 09 11 59 05 34 /058 320 16 70 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
መርከብ ሁ/የገ/ህ/ስ/ማ/ ዩኒየን ኃ.የተ.
Tender details
- Deadline: 2026-07-16
- Publishing entity: Merekeb Farmers' Cooperative Union
- Bid bond: 2%
- Bid document price: 350 (ሶስት መቶ ብር)
- Published: Jul 06, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.