በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ለመስሪያ ቤቱና የፑል አገልግሎት ለሚሰጣቸው ለደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ዞን ፖሊስ መምሪያ እና ለአድማ መከላከል ፖሊስ አገልግሎት የሚውል የተሽከርካሪ ኢንሹራንስ ሽፋን አገልግሎት በኮንትራት ግዢ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል
Description
ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ግ/ጨ/01/2019
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ለመስሪያ ቤቱና የፑል አገልግሎት ለሚሰጣቸው ለደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ዞን ፖሊስ መምሪያ እና ለአድማ መከላከል ፖሊስ አገልግሎት የሚውል የተሽከርካሪ ኢንሹራንስ ሽፋን አገልግሎት በኮንትራት ግዢ በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዢ ለመፈጸም ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ።
1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ሠርተፊኬት ያላቸው፤
3. የግዥው መጠን ብር 200000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. የተሽከርካሪ ሽፋን አገልግሎት ግዢ ፍላጎት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታሰነዱ ማግኘት ይቻላል።
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ከሎ/ፋ/አስ/ዋ ክፍል ቢሮ ቁጥር 9 ማግኘት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ ብር 10000/ አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሰ.ፒ.ኦ/ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ በሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ስም በመክፈል የተከፈለበትን ደረሰኝ ከሰነዱ ጋር አብረው ማቅረብ አለባቸው።
8. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ በሎ/ፋ/አስ/ዋ/ክፍል ቢሮ ቁጥር 9 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16/11/2018 ከጠዋቱ 03፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ በሎ/ፋ/አስ/ዋ/ክፍል በቢሮ ቁጥር 9 በ16/11/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፣
10. በጨረታው የሚሳተፉ ተጫራቾች የአገልግሎት ግዢው በሰሜን ሸዋ ፖሊስ መምሪያ የፑል አገልግሎት ለሚሰጣቸው መ/ቤቶች በኮንትራት ውል ተይዞ የሚፈጸም የአገልግሎት ግዢ በመሆኑ ተጫራቾች በደብረ ብርሃን ከተማ የተሟላ አገልግሎት የሚሰጥ ቅርንጫፍ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል።
11. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው
12. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 9 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በፋክስ ቁጥር 011 681 30 00 በስልክ ቁጥር 011 681 62 06 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።
13. ውድድር የሚደረገው በጥቅል ዋጋ ነው።
የሰ/ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ
Tender details
- Deadline: 2026-07-23
- Publishing entity: በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ
- Bid bond: 10,000.00 (አስር ሺ ብር)
- Bid document price: 300.00 ብር
- Published: Jul 08, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.