መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለፌዴራል ማረሚያ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል የSupply & Fix Signage & Furniture ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል

Description

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር DCE/ SF/92/2026

መከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለፌዴራል ማረሚያ ቤት ግንባታ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውል የSupply & Fix Signage & Furniture ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

የዕቃው አይነት

የፕሮጀክት ስም

የጨረታ ቁጥር

የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት

የጨረታ ማስከበሪያ

Supply & Fix Signage & Furniture

ለፌዴራል ማረሚያ ቤት

DCE/SF/92/2026

 

ሐምሌ 15/2018 . ከቀኑ 415 ሰዓት

ሐምሌ 15/2018 ከቀኑ . 430 ሰዓት

100,000.00

 

ስለሆነም፡-

1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት ( ታከስ ክሊራንስ ) እና የሀገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ… ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2. ተጫራቾች ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ Bid Bond ማቅረብ ይኖርበታል። የጨረታ ማስከበሪያው እንደ ተጫራቹ ምርጫ በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional bank Guarantee) ወይም በባንክ የተሰጠና የተረጋገጠ (CPO) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተዘረዘረው ዝርዝር መሰረት መሆን ይኖርበታል።

4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ መግዛት ይቻላል።

5. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቭሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀን እና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

6. ጨረታው በሰንጠረዡ በተገለፀዉ መሰረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

7. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ቃሊቲ ቶታል ዝቅ ብሎ የቀድሞው መ.ኮ.ድ ግቢ

የቀጥታ ስስክ ቁጥር 0114-40-34-34

ማዞሪያ 0114 42 22-70/71/72

E-mail አድራሻ Info@dce-et.com  

የድህረ ገፅ አድራሻ www.dce-et.com  

ፖ.ሳ.ቁ 3414

የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ


Tender details

  • Deadline: 2026-07-22
  • Bid closing time: 10:15
  • Bid opening: 2026-07-22 10:30
  • Region: Addis Ababa
  • Publishing entity: Defense Construction Enterprise (DCE)
  • Buyer address: ወሎ ሰፈር የቀድሞው ኖሬላ ግቢ
  • Bid bond: 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/
  • Bid document price: 200.00 ብር
  • Published: Jul 08, 2026
  • Posted at: 2026-07-08T08:01:51.000Z

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders