የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት የተለያዩ ዕቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በሁለተኛ (2ኛ) ዙር በሐራጅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል

Description

የሁለተኛ ዙር (2ኛ) ዙር የሐራጅ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት በሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት የባንኩ ደንበኛ የወሰደውን የካፒታል ዕቃ ኪራይ ክፍያ በገባው የሊዝ ውል መሰረት ኪራይ ለመክፈል ፍቃደኛ ባለመሆኑ በባንኩ ስም ተመዝግበው ደንበኛው ተከራይቶ የነበረውን እና ባንኩ ከተከራዩ የተረከበውን የካፒታል ዕቃዎች በሊዝ አዋጅ ቁጥር 103/1990 እና በተሻሻለው የካፒታል ዕቃ ኪራይ አዋጅ ቁጥር 807/2005 በተሰጠው ስልጣን መሰረት ንብረቶቹን ባሉበት ሁኔታ በሁለተኛ (2ኛ) ዙር በሐራጅ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

.

የተከራዩ ስም

የሚሸጠው ንብረት አይነት እና ዝርዝር መረጃ

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻ

የሐራጁ መነሻ ዋጋ (ብር)

ሐራጁ የሚካሄድበት ቦታ

ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት

የሐራጁ ደረጃ

1

አቶ አበበ ሃዋዴ የእርሻ መካናዜሽን አገልግሎት መስጫ

  1. የእርሻ ትራክተር (በቁጥር 01) ብራንድ Massey Ferguson የስሪት ዘመን 2021 አቅም 112HP እና ሞዴል MF6711

2. የእርሻ ማረሻ (በቁጥር 01) ብራንድ OTMA የስሪት ዘመን 2019 ሞዴል O/QD70/E

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሐዋሳ ዲስትሪክት /ቤት ቅጥር ጊቢ ውስጥ ነው።

5,923,887.97

የኢትዮጵያ ልማት ባንከ ሐዋሳ ዲስትሪክት /ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ነው።

ሐምሌ 16 2018 . 400 እስከ 600

2

የሐራጅ መመሪያ ፡-

1. የሐራጁ ተሳታፊዎች የሐራጁን መነሻ ዋጋ 1/4ኛ ወይም 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ሰነድ ሲ.ፒ.ኦ በማቅረብ በሐራጁ ላይ መሳተፍ ይቻላል። በድርጅት ስም የሚጫረቱ ተጨራቾች የድርጅቱን መተዳደሪያ ደንብ ወይም በሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ ጽ/ቤት የተሰጠ የውክልና ሰነድ እና ማንነቱን የሚገልጽ መታወቂያ በማቅረብ ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት በኢትዮጵያ ልማት ባንከ ሐዋሳ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ውስጥ ሐራጅ ጨረታው ይካሄዳል።

2. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም አካል (ግለሰብ፣ ተቋማት ወይም አነስተኛና መካከለኛ ማኅበራት) ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም ተመሳሳይ መብት ያለው ከሆነ ወይም መንግስት በንብረቶቹ ላይ የሚያስከፍለውን የጉምሩክ ቀረጥ ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ ሁሉ በሐራጅ ጨረታው መሳተፍ ይችላል።

3. የሐራጁ አሸናፊ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል። ሆኖምያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በተገለጸው ጊዜ ውስጥ ካልከፈለ ለሐራጅ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጅ ተሰርዞ በድጋሚ የሐራጅ ሽያጩ እንዲወጣ ይደረጋል። በተጨማሪም ንብረቱ ድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚታየው የዋጋ ልዩነት ይጠየቃል፤

4. ማንኛውም ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የንግድ ፈቃድ ያለው የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለውና የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ በሐራጅ ጨረታ መሳተፍ ይችላል።

5. የሐራጁ አሸናፊ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን (VAT) ንብረቶቹን በጥሬ ገንዘብ ወይም እጅ በእጅ ሽየጭ የሚገዛ ከሆነ ከቀረጥ ነጻ መብት የመጠቀም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል። ከቀረጥ ነጻ የመጠቀም መብት ከሌለው በመንግሥት የሚጠየቁ ማንኛውንም ቀረጥ በቅድሚያ በመከፈል ንብረቱን ይረከባል።

6. በሐራጅ አሸናፊ የሆነው ተጫራች የባንኩ አጠቃላይ ተያያዥ የሆኑ ወጪዎችን የመክፈል ግዴታ ይኖርበታል። በተጨማሪም ንብረቱ በገዥው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግሥታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል።

7. በሐራጁ ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ሲ.ፒ.ኦ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል።

8. ባንኩ ለሽያጭ የቀረቡትን ንብረቶች የሚሸጠው እጅ በእጅ በሚደረግ ሽያጭ/cash/ ወይም በባንኩ የሊዝ ፖሊሲ አሠራር በመከተል የሚደረግ ሽያጭ ይሆናል።

9. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሐራጁን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል ሐራጁን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

10. ንብረቶቹን መጎብኘት የሚፈልግ ተጨራች ከጨረታው ቀን በፊት ባሉት ጊዜአት ቀጠሮ በመያዝ ንብረቶቹ በሚገኙበት በሐዋሳ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ውስጥ በአካል በመቅረብ መጎብኘት ይቻላል።

ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 046-180-1528 ደውሎ ማግኘት ይቻላል።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ወላይታ ሶዶ ዲስትሪክት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-23
  • Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
  • Bid bond: 25%
  • Published: Jul 08, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders