ዳዬ በንሳ ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር ለቡና መፈልፈያ ኢንዱስትሪ ግንባታ የሚያስፈልጉ የአካባቢ ዕቃዎችን እና የፋብሪካ አቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Description
ዕቃ ለመግዛት የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ዳዬ በንሳ ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር እና እህት ድርጅቶች ከዚህ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን ለቡና መፈልፈያ ኢንዱስትሪ ግንባታ የሚያስፈልጉ የአካባቢ ዕቃዎችን እና የፋብሪካ አቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
እነርሱም
ሎት 1 -የአከባቢ ዕቃዎች/Local Materials -
1.1 ቀርከህ
1.2 ለጉልቻ የሚሆን ባህርዛፍ
1.3 ፋና፡
1.4 ቅርጮ
1.5 ማገር
1.6 ጠርብ
1.7.ሞራሌ
1.8 ለጉልቻ የሚሆን ጠርብ
2.ሎት፡-2 የፋብሪካ እቃዎች፡-
2.1 ሲምንቶ
2.2 ምስማር
2.3 የቤት ክዳን ቆርቆሮ
2.4 የመብራት ሽቦ
2.5 የመኪና ሸራ (ፕላስቲክ)
2.6 የእጅ ባትሪ (ባለ ቻርጅ)
2.7 አምፖል -60A
2.8 የአምፖል አቃፊ ፡
2.9 የወንፊት ሽቦ
2.10 የአጥር ሽቦ
2.11 ጌት ቫልቭ “ ሲሆኑ ስለ ዕቃዎቹ - ሙሉ ዝርዝሩን
ከጨረታ ሰነድ ላይ ያገኛሉ
በዚህም መሠረት ተጫራቾች ማሟላት ያለባችው መረጃዎች፡-
- ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡና የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ጊዜው ያላለፈበትን ከገቢዎች ሚኒስቴር የተሰጠ ክሊራንስ ወይም የድጋፍ ደብዳቤ እና በግዥ ኤጀንሲ የተሰጠ የአቅራቢነት ማስረጃ ኦርጅናልና ኮፒ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትንና እንዲሁም የትራንስፖርት ዋጋ ጨምሮ መሆኑን መገለጽ አለበት- የታክስ ሁኔታ ያልተገለፀ ከሆነ የቀረበው ዋጋ ማንኛውንም የመንግስት ታክስና ወጪ አካቶ እንደተሞላ ይቆጠራል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ከዋጋ ማቅረቢያ ጋር 10,000 ብር(አስር ሺህ ብር) በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ፋይናንሺያል ኦርጅናል ሰነድ ፖስታ ውስጥ አብረው በማካተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ይህ ጨረታ በአየር ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን በሀዋሳ ከተማ በገብርኤል ቤቴክርስቲያን ፊት ለፊት ከሚገኘው ዳዬ በንሳ ሕንጻ አራተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 12 ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡30 ድረስ በቢሮ በተዘጋጀዉ ሳጥን አስገብተው ጨረታው በዕለቱ 5፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾችት የሚያቀርቡት ዋጋ ቢያንስ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ እስከ 30 ቀናት ድረስ ፀንቶ የሚቆይ መሆኑን መገንዘብ አለባቸው።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን ማለትም የፋይናንሺያል ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ በፖስታ ኤንቨሎፕ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው።
- ስርዝ ድልዝ ያለው የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ተቀባይነት የለውም ከጨረታም ያሰርዛል።
- የመ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡-በሲዳማ ክልል፣ሀዋሳ ከተማ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት በ በሚገኘው
ዳዬ በንሳ ሕንጻ 4ተኛ ፎቅ, ቢሮ ቁጥር 12, ስልክ ቁጥር 09 43 02 77 79
ዳዬ በንሳ ቢዝነስ ኃ/የተ/የግ/ ማህበር
Tender details
- Deadline: 2026-07-18
- Publishing entity: ዳዬ በንሳ ቢዝነስ ኃ/የተወሰነ የግል ማህበር
- Bid bond: 10,000 ብር
- Bid document price: 200.00 ብር
- Published: Jul 08, 2026
Categories
Wood and Wood WorkingBuilding and Finishing MaterialsConstruction and Water WorksPlastic ProductsPlastic Raw Materials and ProductsPlastic Raw MaterialsEquipment and AccessoriesElectrical, Electromechanical and ElectronicsSteel Raw Materials and ProductsSteel, Metals and AluminiumOther MetalsProducts and ServicesAgriculture and FarmingRaw Materials and SuppliesWater Pipes and FittingsAmharic2merkatoዳዬ በንሳ ቢዝነስ ኃ/የተወሰነ የግል ማህበርSidama
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.