በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ደራ ማሎ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት ለጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በካፒታል በጀት ለዋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ እንግዳ ማረፍያ ህንፃ ግንባታ ለመፈፀም የፋብሪካ ዕቃዎችን/የህንፃ መሣሪያዎችን፣ ብሎኬት፣ የጣውላ ውጤቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል

Description

ጨረታ ማስታወቂያ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ደራ ማሎ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት ለጤና ጥበቃ ጽ/ቤት በካፒታል በጀት ለዋጫ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ውስጥ እንግዳ ማረፍያ ህንፃ ግንባታ ለመፈፀም

  • ሎት 1 (አንድ) የፋብርካ ዕቃዎችን /የህንፃ መሣሪያዎችን፣
  • ሎት 2 /ሁለት/ ብሎኬት፣
  • ሎት 3 /ሦስት የጣውላ ውጤቶችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች የተጠቀሱ መስፈርቶችን የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች መጫረት ይችላል።

1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው

2. በዘርፉ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል

3. የቫቲ ተመዝጋቢ የሆነ

4 የንግድ መለያ ቁጥር ያለው

5. በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገበ

6. የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዳቸው ሎት 1 እና ሎት 2 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ ሲፒኦ/ በጥሬ ገንዘብ/ ሎት 3 የጨረታ ማስከበሪያ 5,000 በ/አምስት ሺህ ብር ብቻ/ ጥሬ ገንዘብ ወይም ሲፕኦ ሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ ባንክ ጋራንቲ ማቅረብ የሚችል

ከዚህ በላይ የተጠቀሱትን መሥፈርቶችን የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት 02/11/2018 ቀን ጀምሮ እስከ 16/11/2018 ተከታታይ 15 ቀናት ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር ብቻ/ ደራ ማሎ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት በመክፈል የከፈሉበትን ገቢ ደረሰኝ ኮፒ በመያዝ ደራ ማሎ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት ግዥ ሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 9 በመቅረብ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ።

በመሆኑም ተጫራቾች አንድ ኦርጅናል ፋይናንሻልና 2 ኮፒ ፋይናንሻል ለብቻ ለብቻ ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ፣ ቴክኒካል ሰነድ አንድ ኦርጅናል ውስጥ የጨረታ ማስከበሪያ ተከቶ እና ታሽጎ 2 ኮፒ ሰነድ ለብቻ ለብቻ ታሽጎ በአንድ እናት ፖስታ ውስጥ በትክክል በመሙላት ስም በመፃፍ፣ በመፈረም፣ ማህተም በማሳረፍ፣ አሠሪውን አድራሻ በመፃፍ ኮፒና ኦርጅናል ተብሎ ለብቻ ተጽፎበት ታሽጎ ከላይ የተዘረዘሩ አባሪ ዶክሜንቶች ሁሉ ተደርጎበት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ16ኛ ቀን 17/11/2018 ዓርብ 4፡00 ሰዓት የሚታሸግ ሲሆን የጨረታ ሳጥን የሚከፈተው በዕለቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወክሎቻቸው በተገኙበት ደራ ማሎ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት ይከፈታል። ዕለቱ የሥራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ ሥራ ቀን እና ቦታ ይከናወናል።

መ/ቤቱ የተሸለ ዜዴ ካገኜ ጨረታውን በከፍል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብት አለው። አሸናፊ ተጫራች ዕቃውን የሚያስረክበው የወረዳው ዋና ከተማ ዋጫ ድረስ በማቅረብ ስሆን ርቀቱ ከወላይታ ሶዶ ከተማ 93 ኪሎ ሜትር ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ስልክ 09 16 29 80 13/ 09 10 96 17 84/ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋሞ ዞን ደራ ማሎ ወረዳ ፋይናንስና ፕላን ጽ/ቤት ዋጫ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በጋሞ ዞን ደራ ማሎ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-24
  • Publishing entity: Gamo Gofa Zone Daramalo Woreda F/E/D/Bureau
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር ለእያንዳንዱ
  • Published: Jul 09, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders