የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ለቡና መቁላት፣ መፍጨትና ማሸግ ስራ የሚያገለግሉና ጣሊያን ስሪት የሆኑ ማሽነሪዎችና መሳሪያዎች ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ ለመሸጥ ይፈልጋል
Description
አንደኛ ዙር የሐራጅ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት ከአቶ ብሩህ ተስፋ ጥሩነህ ባልተከፈለ ዕዳ ምክንያት በአዋጅ ቁጥር 103/1990 እና 807/2005 መሰረት የተረከባቸውንና ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለጹትን ለቡና መቁላት፣ መፍጨትና ማሸግ ሰራ የሚያገለግሉና ጣሊያን ስሪት የሆኑ ማሽነሪዎችና መሳሪያዎች ባሉበት ሁኔታ በሀራጅ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የንብረቱ ዝርዝር |
ብዛት በቁጥር |
የሐራጅ መነሻ ዋጋ |
የንብረቱ ሁኔታ |
ሐራጁ የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
|
1 |
Pneumatic Loader Model -ELP60 |
1 |
84,205,883.24 |
አዲስ |
ነሀሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት |
|
2 |
Coffee Roaster Model -TTG60 |
1 |
|||
|
3 |
Roasted Coffee Receiving Hopper |
1 |
|||
|
4 |
Loader (Pneumatic Conveyor system |
1 |
|||
|
5 |
Suction Pump group for Pneumatic conveyor system |
1 |
|||
|
6 |
Silos for roasted coffee beans |
2 |
|||
|
7 |
Drop diverter valve |
2 |
|||
|
8 |
Additional Unit of Pneumatic conveyor to feed the roasted coffee beans to packing machine |
1 |
|||
|
9 |
Coffee Grinder Model-MAIN 300 |
1 |
|||
|
10 |
Raking Screw Conveyor to feed the ground coffee to silo |
1 |
|||
|
11 |
Ground Coffee Silo |
1 |
|||
|
12 |
Electric Control Panel |
1 |
የሐራጁ መመሪያ
1. ንብረቱን መግዛት የሚፈልግ ተጫራች የሀራጁን መነሻ ዋጋ 1/5ኛ (20%) ብር 16,841,176.65/አስራ ስድስት ሚሊዮን ስምንት መቶ አርባ አንድ ሺ አንድ መቶ ሰባ ስድስት ብር ከ65/100 ሳንቲም/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በማቅረብ በሀራጁ መሳተፍ ይችላል። ተጫራቹ አሸናፊ ከሆነ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ከንብረቱ የመሸጫ ዋጋ ላይ /ተጫራቹ ካሸነፈበት ዋጋ ላይ/ የሚቀነሰ ይሆናል።
2. ንብረቱ በሲዳማ ብ/ክ/መንግስት ይርጋለም ከተማ፣ ይርጋለም አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ በሚገኘው ሺድ ውስጥ ይገኛል።
3. የሚሸጠው ንብረት የገባው ከቀረጥ ነጻ ሲሆን ገዥው የቀረጥ ነጻ መብት ተጠቃሚ እንዲሆን ባንኩ ድጋፍ ያደርጋል። ፈቃዱን ካላገኘ ግን የቀረጥ ከፍያው በገዥው ይፈጸማል።
4. ንብረቶቹን ሙሉ በሙሉ በካሸ/ በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ ተጫራች የንብረቱ የሸያጭ ዋጋ ላይ 15% ተእታ (VAT) እና ሌሎች ገዥው በሕግ እንዲከፍላቸው የተወሰነ ታክስ ክፍያን ጨምሮ ይከፍላል።
5. የሐራጁ አሸናፊ ባንኩ ማሸነፉን በደብዳቤ ከገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል። የሀራጁ አሸናፊ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀሪውን ገንዘብ አጠቃሎ ካልከፈለ ጨረታው ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ሐራጁ በድጋሚ ይካሄዳል፡፡ ለተሸነፉ ተጫራቾች ለሀራጁ ያስያዙት ገንዘብ ወዲያወኑ ይመለስላቸዋል።
6. ተጫራቹ በከፊል ዱቤ ለመከራየት አሸናፊ ከሆነ ባንኩ ማሸነፉን እንዲያውቅ ካደረገበት ቀን ጀምሮ በአንድ ወር ውስጥ የባንኩን የማሸነሪ ኪራይ መሰፈርት በማሟላት እና የሚጠበቅበትን ቀሪ ክፍያ አጠቃሎ በመከፈል የማሽነሪ ኪራይ ውል መፈረም ይኖርበታል። በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ የጨረታ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ለጨረታው ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይደረጋል።
7. የካፒታል ዕቃውን ካለበት መጋዘን ወደ ሚፈልግበት ቦታ የማጓጓዣ ወጪ፣የጉዞ ኢንሹራንስ፣የመትከያ፣ስራ የማስጀመሪያና ተያያዥ ወጪዎችን ገዥው/ተከራይ ይሸፍናል።
8. ሐራጁ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነሀሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም. ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ንብረቶቹ በሚገኙበት አድራሻ ይካሄዳል።
9. ስለ ንብረቱ ሁኔታ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር +251 46 221 2789 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል።
10. ንብረቱን ለመጎብኘት ከሀዋሳ ዲስትሪክት ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጎብኘት ይቻላል።
11. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሀራጁ አይገደድም።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሀዋሳ ዲስትሪክት
Tender details
- Deadline: 2026-08-11
- Publishing entity: Development Bank of Ethiopia
- Bid bond: 20%
- Published: Jul 09, 2026
Categories
Source
2merkato
Always verify against the original notice before bidding.