የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የተለያዩ የግንባታ ግብዓቶችን በግልፅ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል

Description

የተለያዩ የግንባታ ግብዓቶች ግዥ ግልጽ ጨረታ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር የኮ/ ዲ/ግ/ማ /ድ/ግ/ ጨ/ቁ 28/2018

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት የሚከተሉትን የግንባታ ግብዓቶች ከዚህ በታች በሎት ተከፍሎ በተቀመጠው መሰረት በግልፅ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።

  • ሎት 1፡- የሳኒተሪ ዕቃዎች
  • ሎት 2፡- የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣
  • ሎት3፡- አልሙኒየም ፕሮፋይል ከነመገጣጠሚያ
  • ሎት 4፡- ቴምፐርድ ግላስ supply and fix

ስለሆነም፡-

1. በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስችል በዘርፉ የተሰጠ የታደሠ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ፤ የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ኮፒ አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ ድርጅቶችና ግለሰቦች የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ) ብር በመክፈል በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት ቢሮ በመቅረብ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ።

2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 1 ብር 200,000.00(ሁለት መቶ ሺህ ብር) ለሎት 2 ብር 200,000.00(ሁለት መቶ ሺህ ብር) ሎት3 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) ሎት4 100,000.00/ አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የ90 ቀናት የባንክ ዋስትና (unconditional bid bond guarantee) ከሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ጋር በማያያዝ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

3. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ ሆኖ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰአት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ተሳታፊዎች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።

4. የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ግንባታና ማማከር ድርጅት የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቃሊቲ ማሰልጠኛ ፊት ለፊት የኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ቢሮ አጠገብ

ስልክ ቁጥር፡-09-20-11-75-60

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮንስትራክሽን ዲዛይን፣ ግንባታና ማማከር ድርጅት


Tender details

  • Deadline: 2026-07-20
  • Publishing entity: Addis Ababa Administration Construction Design, Building and Consultancy Organization
  • Bid bond: በየሎቱ የተለያየ ነው
  • Bid document price: 300.00 ብር
  • Published: Jul 09, 2026

Categories

Source

2merkato

Always verify against the original notice before bidding.

View original ↗
← Back to all tenders